«ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ፤ ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው»(መዝ.119፡125)

«ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ፤ ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው»(መዝ.119፡125)

የሰው ልጅ ያሰበው ሀሳቡ የሚሳካለት፣ ያቀደው ዕቅድ የሚፈጸምለት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሲከናወንለት ብቻ እንደሆነ በዚህ ታሪካዊ የሰላም ጉባኤ የተረጋገጠ እውነታ ነው።

ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለዓመታት የዘለቀው መለያየት በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠረና ግቡም ብዙም ያልታሰበበት ቢሆንም መለያየቱ ግን ብዙ ዋጋ ያስከፈለ፤ ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ የጎዳና የታሪክ ጠባሳን ያኖረ ነው። በዚህ ልዩነት ምክንያት አባቶች ሆድና ጀርባ ሆነዋል ቤተሰብም ተለያይቷል። በአንድ ሃይማኖት ሆነን፣ በአንድ ሥርዓተ አምልኮ እያመለክን፣ በአንድ ቋንቋ አገልግሎት እየሰጠን ሆኖም ግን ተለያይተን ተኳርፈናል፣ ተካሰናል፣ ፍርድ ቤት ቆመናል፣ ገበናችንን ለባዕዳን፣ ገንዘባችንን ለጠበቆች፣ ጉልበታችንን ለብክነት አውለናል። ይህ ሁሉ ኪሣራ በልዩነት ምክንያት ያገኘን ኪሣራ ነው።

ይህንኑ በመገንዘብ ሁለቱም ወገኖች (አባቶቻችን) የአንድነትና የሰላም መፍትሔን ለማምጣት ብዙ ጊዜ ሲደክሙበት እንደቆዩ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ቀን ስላልደረሰ እስከ አሁን ቆይቶ አሁን ጊዜው ሆኗል(ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ነውና)። እኛም በጊዜያችን ይህ ነገር ሲከናወን ምሥክር ለመሆን ስላበቃን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

Read More

በገለልተኛ አስተዳደር ላለፉት 18 ዓመታት ይተዳደር የነበረው የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለመግባት ወሰነ፤ ለብፁዕ አቡነ ዘካርያስም ጥያቄውን በደብዳቤ አቀረበ

በገለልተኛ አስተዳደር ላለፉት 18 ዓመታት ይተዳደር የነበረው የደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ለመግባት ወሰነ፤  ለብፁዕ አቡነ ዘካርያስም ጥያቄውን በደብዳቤ አቀረበ

በደብዳቤአቸውም «በእናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ በመሆን አጥተነው የነበረውን የልጅነት በረከትና ክብር፣ ርቆን የነበረውን የብፁዕነትዎ እና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ቡራኬ ማግኘት የምንችልበት ደረጃ ላይ መቆም እንደሚገባን እና በዚህ መንገድ እየተጓዝን የቤተ ክርስቲያናችንን ተልእኮ ለማፋጠን ከብፁዕነትዎና በብፁዕነትዎ ከሚመራው ሀገረ ስብከት፣ እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተ ክህነትና ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጣውን መመሪያ አክብሮ በማስከበር የልጅነት ድርሻችንንና ግዴታችንን ለመወጣት በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረ,ት ላይ አውጀን በይፋ ተቀብለናል። ተግባራዊ ለማድረግም በመንፈሳዊ ቁርጠኝነት የብፁዕነትዎ ጸሎት እየረዳን እንቀጥላለን» ብለዋል።

Read More

ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በዊስከንሰን ግዛት ሚልዋኪ ከተማ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልካም ፈቃድ በቅርቡ አገልግሎት ይጀምራል

ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በዊስከንሰን ግዛት ሚልዋኪ ከተማ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልካም ፈቃድ በቅርቡ አገልግሎት ይጀምራል

በባዕድ ምድር በስደት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በሄዱበት ሁሉ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዳይዝሉ ከራሳቸው ቤት አስቀድመው የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ልባቸው ሁልግዜም የተነሳሳ በመሆኑ በሀገረ ስብከታችን ውስጥ በዊስከንሰን ግዛት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላለፉት ሁለት ዓመታት በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በጽዋ ማኅበር እየተሰባሰቡ ቃለ እግዚአብሔርን ሲማሩ ከቆዩ ከሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ጋር መደበኛ ውይይቶችን ሲያደርጉ ቆይተው ይህንን ስብስባቸውን ከፍ ወደአለ ደረጃ በማሳደግ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ አሁን ለግዛቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት በቅተዋል።

የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስም ሁኔታውን በአግባቡ መርምረው ይህ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሠረት ፈቃድ ሰጥተዋል። ለአስተባባሪዎች በላኩላቸው የፈቃድ ደብዳቤ እንደገለጹትም «የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት መመረጥ ለጥቂቶች ብቻ የሚሰጥ መንፈሳዊ ዕድል መሆኑን ተገንዝባችሁ በማይጠቅም ብልሃት የተፈጠረውን የዓለም ተረት ሳትከተሉ አባቶቻችሁ በሠሩት ጎዳና እየሄዳችሁ፣ በማስተዋልና ከሀገረ ስብከቱ የሚሰጠውንም መመሪያ ተቀብላችሁ ተግባራዊ ለማድረግ በጎ ኅሊናን ገንዘብ በማድረግ እየተጋችሁ ይህንን ሃሳባችሁን ዳር ታደርሱት ዘንድ እኔም በጸሎት አስባችኋለሁ» በማለት አባታዊ አደራቸውን አሳስበዋል።

አያይዘውም «አስፈላጊ የሆኑ ንዋያተ ቅድሳትን እያሟላችሁና እያደራጃችሁ ኃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ እያሳሰብሁ ቤተ ክርስቲያናችሁም ቅድስት ልደታ ለማርያም እንዲሆን ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኗል» ሲሉ ገልጸዋል።

ሀገረ ስብከቱም ይህንን ተግባር በማተባበር ለደከሙት አሁን ላሉትም ሆነ ከዚህ ቀደም ለነበሩት ምእመናን እንኳን ደስ አላችሁ እያለ እንደስካሁኑ ሁሉ ወደፊትም የሚገባውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ዶ/ር ሙሴ ሐረገወይን ለአስተባባሪዎች ቃል ገብተዋል።

Read More

ስለ ቦስተን መንበረ ልዑል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ - ወቅታዊ መረጃ

ስለ ቦስተን መንበረ ልዑል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ - ወቅታዊ መረጃ

ለቤተ ክርስቲያን ሕግና ለአጥቢያቸው መተዳደሪያ ደንብ አንገዛም ፣ ብሎም ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስም አንታዘዝም ባሉ  ምእመናን ምክንያት ለዓመታት የቦስተንና አካባባዊው ምእመናን አገልግሎት ያገኙበት የነበረው የመንበረ ልዑል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በፍርድ ቤት ውዝግብ ምክንያት መዘጋቱ ይታወሳል።

ሀገረ ስብከቱ የጉዳዩን ሕገወጥነት በተደጋጋሚ በማስረዳረዳት አጥፊዎቹ ታርመውና አለአግባብ በድምጽ ብልጫ አሰናብተናቸዋል ያሉትን አስተዳዳሪ ወደቦታቸው መልሰው፣ የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ የሰበካ ጉባኤ አባላትም በምትካቸው አስመርጠው በሰላም እንዲገለገሉ ሀገረ ስብከቱ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። እኒህ ሕገ ወጥ አካላት ግን የቀረበላቸውን አማራጭ ሁሉ አንቀበለም በማለታቸው ምክንያት ካህናት እና ምእመናን ያለ አገልግሎት ለወራት መንገላታታቸው አግባብ ባለመሆኑ የፍርድ ቤቱ ጉዳይ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ በሥርዓት የሚሄዱት ወገኖች በሌላ ቦታ አገልግሎት እንዲሰጡ እና እንዲያገኙ በተፈቀደላቸው መሠረት አገልግሎት ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥሯል።

ፍርድ ቤቱ ጊያዊ ብይን ሰጥቶባቸው ከነበሩት ጉዳዮች አንዱ አዲስ በመሠራት ያለው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ ሁለቱም ወገኖች መገልገል እንደማይችሉበት መወሰኑ ነው። በፍጹም ማን አለብኝነት መንፈስ የተያዙት አካላት ግን የፍርድ ቤቱን ሕግ በመተላለፍ ወደ አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ገብተው አገልግሎት ሊጀምሩ እንደሆነ ሲሰማ ሕጋዊያኑ አገልጋዮችና ምእመናን ለፍርድ ቤቱ በማሳዎቃቸው ምክንያት ፖሊስ ይህንን ሕገ ወጥ ተግባራቸውን በማገጃ አስቁሞታል።

Read More

ለአይዋ የመጀመሪያው ለኒውዮርክ ሀገረ ስብከት 34ኛ የሆነው ደብረ ሰላም ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተተከለ

ለአይዋ የመጀመሪያው ለኒውዮርክ ሀገረ ስብከት 34ኛ የሆነው ደብረ ሰላም ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተተከለ

በአይዋ ግዛት ሱ ሲቲ ከተማ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ከሀገረ ስብከቱ ጋር በመተባባር ለመጨረሻው ምእራፍ ያደረሱት የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልካም ፈቃድ ዛሬ ቅዳሜ የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በመልአከ አርያም ቆሞስ አባ ኃዕለሚካኤል ሙላት የሚኒያፖሊስ ርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ። በዚህ በዓል ላይም የከተማው ምእመናን እስከዛሬ ድረስ ለሁለት ሰዓት የመኪና ጉዞ እየሄዱ አገልግሎት ያገኙ የነበረበትና ለአሁኑ ውጤትም ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከቱት የደብረ መንክራት ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ መንክራት ቀሲስ አበበ ላመስግን እንዲሁም ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ሄኖክ ያሬድ ከርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲሁም ቀሲስ ምዑዝ ከዲሞይን አይዋ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተዋል።

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ፲፯ ዓመታት በሊቀ ጳጳስነት ያስተዳደሩትን የአርባምንጭን ሕዝብ ለመባረክ አርባምንጭ ሲገቡ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ፲፯ ዓመታት በሊቀ ጳጳስነት ያስተዳደሩትን የአርባምንጭን ሕዝብ ለመባረክ አርባምንጭ ሲገቡ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ፲፯ ዓመታት በሊቀ ጳጳስነት ያስተዳደሩትን የአርባምንጭን ሕዝብ ለመባረክ አርባምንጭ ሲገቡ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በ፳፻፱ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለመገኘት አዲስ አበባ ገቡ

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በ፳፻፱ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለመገኘት አዲስ አበባ ገቡ

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በ፳፻፱ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለመገኘት ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገቡ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እንዲሁም ሌሎች አባቶች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Read More

የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ምእመናን እና ካህናት 1.6 ሚሊዮን ብር አዋጥተው ወደ ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በመላክ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ቃል እንዲከበር አደረጉ።

የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ምእመናን እና ካህናት 1.6 ሚሊዮን ብር አዋጥተው ወደ ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት በመላክ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ቃል እንዲከበር አደረጉ።

የብፁዕነታቸውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ በሀገረ ስብከታቸው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን እና ካህናት ያዋጡትን አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር ይዘው የመጡት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን / ሙሴ ሐረገወይን እና የሚዲያና ኮሚዮኒኬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ሠናይ ምንውየለት ረቡዕ ሚያዚያ ፳፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት አቅርበዋል። በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተመራው በዚህ ስብሰባ የወቅቱ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ጤሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እንዲሁም የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማርቆስም በስብሰባው ተገኝተዋል።

                             ==========  ለዝርዝሩ ቪዲዮውን ይመልከቱ ===========

Read More

መጋቢት መድኃኔዓለም ንግሥ አከባበር

+++ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ+++

እስከ አድአሚሃ ለጽዮን ወእስከ ዘሙሴ ደወል።
የአቅቡ ነግሀ በመዋዕል።
ከመ ካልአን አግብርተ ምድር የአቅብዎ ለሰብል።
መድኃኔዓለም አማኑኤል።
እይብልዑ ነግሀ ፍሬሁ ሀለፍተ ሙስና ወሀጉል።
ተሐጽረት በሦከ መከራ ዲምኀከ ዕክል።
ጽርሐ አርያም ጽዮን ቤተ ሥላሴ ወቤተ ማርያም ድንግል።
ጽርሐ አርያም ጽርሕ ልዕልና ምስባከ ሐዲስ ወንጌል።
ጽርሐ አርያም ደብረ ቤቴል።
ጽርሐ አርያም ተሠምየት መንበረ ልዑል።
ቅድመ ኵሉ በብርሃን ጽዱል።

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍን ይቅርታ ተቀብለው አስተላልፈውበት የነበረውን እገዳ አነሡለት

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍን ይቅርታ ተቀብለው አስተላልፈውበት የነበረውን እገዳ አነሡለት

በመሆኑም ልጃችን ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ባጠፋው ጥፋት ፍጹም በመጸጸት፣ የባልንጀሮቹን ምክር በመስማት እንደ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ከእኔ ከክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ጋር በፍጹም ትኅትና በመነጋገር ይቅርታን ስለጠየቀ በቁጥር 144/2009 መጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. አስተላልፍነው የነበረውን የሥልጣነ ክህነት እገዳ ሙሉ ለሙሉ አንሥተን ከቅድስተ ቅዱሳኑ ጀምሮ ባለው የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት በሙሉ በነበረው ክብር ያገለግል ዘንድ ከታላቅ ክብር ጋር እግዱን ያነሳንለት መሆኑን እናሳውቃለን። አንተን ልጃችንንም ይህንን ተግሣጽ ተቀብለህ በመመለስህ ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሃለች። ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ዛሬም ይሁን ወደፊት ወደ ሀገረ ስብከታችን በሚመጣበት ጊዜ በሀገረ ስብከታችን በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲያገለግል የፈቀድንለት መሆናችንንም ጨምረን እናሳውቃለን።

Read More

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍም እና ቀሲስ አንዱዓለም ዳግማዊን ይመለከታል

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍም  እና ቀሲስ አንዱዓለም ዳግማዊን ይመለከታል

በቦስተን እና አካባቢው ላላችሁ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን
ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች

ከዚህ ቀደም ብለን በቁጥር 136/2016 January 27, 2016 በተጻፈ ደብዳቤ እንዳሳወቅነው ቅዱስ ሲኖዶስ እና ሀገረ ስብከቱ ሳይፈቅድ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ በቦስተን ከተማ «ደብረ ብርሃን ሥላሴ» ብለው ቤተ ክርስቲያን አቋቁሜአለሁ በማለታቸው ሥልጣነ ክህነታቸው ሙሉ በሙሉ መታገዱን ማሳዎቃችን ይታወሳል። በዚህም ተግባራቸው ለሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ንቀት ከማሳየታቸውም በላይ የቦስተን ምእመናን የጥርና የሐምሌ ሥላሴ እየመጡ የሚሳለሙትን፣ ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ልዩ ትኩረት የተሰጠውን እና መንበረ ጵጵስና የሆነውን የኒውዮርክ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን ተገዳድረዋል።

ሥልጣነ ክህነታቸው ከታገደ በኋላም ለተለያዩ ካህናት የአገልግሎት ግብዣ ጥሪ ሲያቀርቡ «ሥልጣነ ክህነትዎ ስለታገደ አብረንዎት አናገለግልም» በመባላቸው ምክንያት አሁን ደግሞ ፊታቸውን በስደተኛው ክፍል እናገለግላለን ወደሚሉ ካህናት በማዞር መጋቢት ፪ እና ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ከስደተኛው ክፍል ቀሲስ አንዱዓለም ዳግማዊን እና በቅርቡ ከኢትዮጵያ የመጣውን ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍን በመጋበዝ ጉባኤ በማዘጋጀት ምእመናንን ማደናገሩን ቀጥለውበታል።

ቀሲስ አንዱዓለም ዳግማዊ ዛሬ አሜሪካ መጥቶ ስደተኛውን ክፍል ከመቀላቀሉ በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክህነት ሰጥታ፣ ከአሏት መንፈሳዊ ተቋሞቿም ዋነኛ በሆነው በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተምራ እና መምህር ብላ ማዕረግ ሰጥታ ለክብር አብቅታዋለች። ሊተገብረው ዳገት በሆነበት የሕግ መጽሐፍ ላይ «ያለ ሊቀ ጳጳስ የምትኖር ቤተ ክርስቲያን እንደ ፈት ናት» የሚለውን የተማረው ቀሲስ አንዱዓለም እኔ ከስደተኛው ወገን ስለሆንኩ ማንም አይነካኝም በሚል የሰነፍ አስተሳሰብ ሥልጣነ ክህነቱ ከታገደ ጋር በአገልግሎት መተባበርን እንደመረጠ እንረዳለን። ሆኖም ግን እርሱ አክብሮ አይያዘው እንጂ ሥልጣነ ክህነቱን የተቀበለው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ስለሆነ ይህንንም ክህነት የማገዱ ሥልጣን አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ነው። ከስደተኛው ወገን ነው በሚል ቸላ ሳንል በዚህ የድፍረት ተግባር እንዳይተባበር ብንመክረውና ብናዝዘውም እምቢ ብሎ የሊቀ ጳጳሱን ትዕዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ሥልጣነ ክህነቱን ሙሉ ለሙሉ አግደናል።  ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ከጣሱ እና ከተወገዙ ካህናት ጋር በመተባበር ቤተ ክርስቲያንን እንዳይበድል በተደጋጋሚ ያሳሰብነውን፣ የመከርነውን እና ያዘዝነውን አቃልሎ ከተወገዙ ካህን ጋር በአገልግሎት በመተባባሩ ከዛሬ ጀምሮ ሥልጣነ ክህነቱን አግደናል። በዚህ ጥፋቱ ተጸጽቶ ይቅርታ የሚጠይቅ ከሆነ ወደፊት የሚታይለት ይሆናል።

Read More

« ኢታርምም ወኢትደመም እግዚኦ - ጌታ ሆይ ዝም አትበል አቤቱ ቸልም አትበል» መዝ ፹፪(፹፫)፣፩ « እስመ ናሁ ዘአንተ ሠራዕከ እሙንቱ ነሠቱ - ምክንያቱም አንተ የሠራኸውን ሕግ እነርሱ አፍርሰውታልና» መዝ ፲(፲፩)፤፫

« ኢታርምም ወኢትደመም እግዚኦ - ጌታ ሆይ ዝም አትበል አቤቱ ቸልም አትበል» መዝ ፹፪(፹፫)፣፩ « እስመ ናሁ ዘአንተ ሠራዕከ እሙንቱ ነሠቱ - ምክንያቱም አንተ የሠራኸውን ሕግ እነርሱ አፍርሰውታልና» መዝ ፲(፲፩)፤፫

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሲኖዶሳዊ አቋም በመጻረር በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በማይፈቅደው መልኩ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና እንመሠርታለን ስለሚባለው ማኅበረ ካህናት የሚመለከት ይሆናል።

. . .

የፈተና መምጫው መቼና ከየት  እንደሆን አይታወቅምና በቀድሞው መንግሥት ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ « መላው የኢትዮጵያ ካህናት ማኅበር (መ/ኢ/ካ/ማ)» የሚባል ድርጅት ተቋቁሞ እንደነበር በታሪክ ብቻ የምናውቀው ሳይሆን የዓይን ምስክርም በመሆናችን ጉዳዩን በስፋት እናውቀዋለን። ይኽ መ/ኢ/ካ/ማ በመባል የሚታወቀው ማኅበር እንደ ሙያ ማኅበራት እንደ አንዱ ሆኖ ተጀምሮ ወደፊት የሚያመጣው ችግር አደገኛ መሆኑን በማወቅ ሳይውል ሳያድር መፍትሔ እንዲገኝለት ሦስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት የጉዳዩን አሳሳቢነት ለሊቃነ ጳጳሳቱ ይፋ አድርገው እርምት እንዲሰጥበት አድርገዋል። በመልእክታቸውም የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን አካሄድ ሊያዛባ የሚችልና እኛ ሥራውን ልንከታተለው የማንችለው በራሱ የሚመራ የካህናት ማኅበር ሊቋቋም ስለማይገባው እንዲህ ያለው አካሄድ ስር ሳይሰድና ወደፊት ብዙዎችን በዚህ መረብ ውስጥ እያስገባ እንዳያጠምድ ከወዲሁ መገታት ስለሚኖርበት ይኼንን የተዛባ መንገድ እንቃወመዋለን፤ እናወግዘዋለንም በማለት ውሳኔ እንዲሰጥበት አስደርገዋል። በተላለፈው ሲኖዶሳዊ ውሳኔ መሠረትም የሚመለከተውን የመንግሥት አካል በማነጋገር ቅዱስ ሲኖዶስ ከአመሠራረቱ ጀምሮ የማያውቀውን ማኅበረ ካህናት (መ/ኢ/ካ/ማ) ማስቆም ችሏል። ቅዱስነታቸው ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር መክረው ይኽንን አደገኛ ጎዳና ያስቆሙት የካህናትን ኅብረት በመቃወም ሳይሆን ሰንሰለት የሌለውና እርከኑን ያልጠበቀ አካሄድ ነገ የሚያመጣውን ችግር በመመልከት ነው።

 ዛሬም አንድነት ፈጥረን ኅብረት ኖሮን እንቁም በሚል ሰበብ በሰሜን አሜሪካ በተለይም በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ያሉ እና በእኛ ሀገረ ስብከትም ያሉ የዚሁ ስሜት ተጋሪ ከሆኑ አንዳንድ ካህናት ጋር በመሆን እየተመሠረተ ያለው ማኅበረ ካህናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው በመሆኑ መሥራቾቹ አካሄዳችሁን ከወዲሁ ሊገቱ እና እርምት ሊሰጡበት ይገባል። መሰባሰቡ ባይከፋም ይኽንን የካህናት ማኅበር ሊቋቋም፣ ሊመራና ክትትል ሊደረግበት የሚገባው እንደ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አካሄድ ከቅዱስ ሲኖዶሱ በተመደበ ሊቀ ጳጳስ መሆን ይገባዋል እንጂ ከላይ ከላይ የተነገረ አመለካከቱ ብቻ ቀና ነው በሚል ሰበብ ቀዳዳ ማበጀት ተገቢ አይደለም። እርከኑን የጠበቀ መሪ ሳይኖረውና ተጠሪነቱ ለማን እንደሆን ሳይታወቅ ማኅበር መመሥረት ያለ ምንም ጥርጥር ነገ ለብቻዬ መቆም ችያለሁ በሚል አንድምታ ለቅዱስ ሲኖዶስ የማይታዘዝ አካል መሆኑ አይቀሬ ነውና።

Read More

የሀገረ ስብከቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በቺካጎ ተካሄደ፣ መጪው ጉባኤም በሚኒያፖሊስ እንዲሆን ተወሰነ

የሀገረ ስብከቱ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በቺካጎ ተካሄደ፣ መጪው ጉባኤም በሚኒያፖሊስ እንዲሆን ተወሰነ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምሥራቅ፣ ደቡብ ምሥራቅ እና መካከለኛው አሜሪካ ኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስተዳደር እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በተገኙበት ከኅዳር ፲፬ እስከ ኅዳር ፲፭ በቺካጎ ከተማ ተካሄደ።

ይህ ጉባኤ ሐሙስ ጠዋት ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. በቺካጎ ደብረ ኤዶም ደብረ ገነት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ካቴድራል በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መሪነት ጸሎተ ኪዳን በማድረስ እንዲሁም የዕለቱን ወንጌል ሉቃስ ወንጌል ምእራፍ ፪፣ ፵፩ - ፶፪ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ተርጉመው በስፋት ካስተማሩ በኋላ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪጅ ሊቀ ማእምራን ቀሲስ ዶ/ር ሙሴ ሐረገወይን አወያይነት ጉባኤው ተከፍቷል።

በቅድሚያም በ35ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በጥቅምት 2009 ዓ.ም. በሀገረ ስብከታችን ተወክለው የተገኙት መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ማርቆስ ረታ (ርዕስ አድባራት ደብረ ብርሃን ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል፣ ኦሃዮ) እና መልአከ አርያም ቆሞስ አባ ኃይለ ሚካኤል ሙላት (ርዕስ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ ሚኒሶታ) ወጪያቸውን የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሸፍነው በመሄድ የሀገረ ስብከታችንን ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴ ያቀረቡት ሪፖርት ለዚህ ጉባኤ በሊቀ ማእምራን ቀሲስ ዶ/ር ሙሴ ሐረገወይን - የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪጅ አማካኝነት በንባብ ቀርቧል።

Read More

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ከአገልግሎት ታገዱ የሃያ አንድ ቀን የጊዜ ገደብም ተሰጣቸው

መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ከአገልግሎት ታገዱ የሃያ አንድ ቀን የጊዜ ገደብም ተሰጣቸው

በዳላስ «ስደተኛ ሲኖዶስ» ነን ከሚሉትም ሆነ በሚኒያፖሊስ የቀድሞው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ውጉዛን ካህናት ጋር በአገልግሎት ከተሳተፉ በኋላ «ቅዳሴውን ሰምተናል፣ ሁሉንም ተመልክተናል። ከኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አንድም የጎደለ ነገር አላገኘሁም። የልምድ አዋላጅ ሰባኪ፣ ከማዞሪያ ላይ የተሳፈርሁም አይደለሁም። ከሰባት ዓመቴ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ነው የኖርሁት። ሁሉን አውቀዋለሁ። አንድም የጎደለ ነገር የለም (የሚታይ ካልሆነ በስተቀር) አንድም የጎደለ የለም» ሲሉም ተደምጠዋል።
•    ከሰባት ዓመትዎ ጀምሮ ያስተማረችዎት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ ተላልፈህ ባልተፈቀደ ቦታ ቁም ብላ አላስተማረችዎትም፤
•    ከሰባት ዓመትዎ ጀምራ ያስተማረችዎ ቤተ ክርስቲያን ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ከገበያ በሚገዛ የደምበጃን ወይን ሲተካ ይህ ምንም ችግር የለውም የጎደለ ነገር የለውም ብላ አላስተማረችዎትም፤  
•    ከሰባት ዓመትዎ ጀምሮ ያስተማረችዎት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የተአምሯ መጽሐፍ «የሚረብሽ መጽሐፍ ነው» በሚባልበት እና ስሟ በተነቀፈበት ቦታ መገኘት ምንም ችግር የለውም የጎደለ ነገር የለውም ብላ አላስተማረችዎትም፤  
•    ከሰባት ዓመትዎ ጀምራ ያስተማረችዎ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ያሬድ የምስጋና ዝማሬ እና ቅዳሴያቱም በኦርጋን ቢቀርቡ የሚያጎድለው ነገር የለም የተሟላ ነው ብላ አላስተማረችዎትም፤   
•    ከሰባት ዓመትዎ ጀምራ ያስተማረችዎ ቤተ ክርስቲያን ከተወገዘ ካህን ጋር በአገልግሎት መሳተፍ፣ ሦስት እና አራት መሥመር እየዘለሉና የመንፈስ ቅዱስን ቃል እየሻሩ እንቀድሳለን ከሚሉት ጋር መተባባር ራስንም እንደሚያስወግዝ እንጅ ምንም የጎደለ ነገር የሌለበት ነው ብላም አላስተማረችዎትም።  

 

ሙሉውን ለማንበብ PDF

Read More

ጉዳዩ፦ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁን ይመለከታል

ጉዳዩ፦ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁን ይመለከታል

እምነት እና ሥርዓትን ለደቀ መዛሙርት ከማስተማር በፊት አንድ መምህር ራሱ ሥርዓቱን እና ሕጉን ሳይከፍልና ሳይቀንስ ሊያምን እና ሊፈጽም ሲገባው መጋቤ ሐዲስ ግን ቤተ ክርስቲያኗ እና ምእመናን የሰጠቻቸውን የክብር ቦታ ለራስ ሃሳብ ማስፈጸሚያ ማዋልን መርጠዋል። ስለሆነም ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በክብር ተስተናግደው በሄዱበት ሀገረ ስብከት ዛሬ ይህንን ለማድረግ የወሰኑበትን ምክንያት እንዲያስረዱ የተሰጣቸውን ዕድል ተጠቅመው እስኪያስረዱ ድረስና ይህንንም የሚገልጽ ደብዳቤ እስከሚደርሳችሁ ድረስ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ በሀገረ ስብከታችን ውስጥ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ማስተማር እንደማይችሉ ተገንዝባችሁ እርሳቸውን ከመጋበዝም ሆነ እንደዚያ ያለ ጉባኤ ከመሳተፍ እንድትቆጠቡ በአጽንዖት እናሳስባለን።  

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ዘመን መለወጫን እና የሀገረ ስብከቱ ዌብ ሳይት መጀመርን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ዘመን መለወጫን እና የሀገረ ስብከቱ ዌብ ሳይት መጀመርን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪም የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ሁላችሁ! የዘመናት ጌታ የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ እያልኹ ይኽንን የከበረ አባታዊ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።

...

በዚህ የዘመን መቁጠሪያ አጽዋማት፣ በዓላት፣ አውራኅ፣ ዓመታት እና ቀኖች እነዚህ ሁሉ የሚውሉበት አጠናቅቀው ያውቁበታል። በዚህም የምኅላ ቀናት፣ የጸሎት ቀናት፣ የበዓላት ቀናት ብለው ለይተው ያውቃሉ፤ እግዚአብሔርንም ይማልዱበታል። ይህ በአጠቃላይ ትርጉሙ ባሕረ ሃሳብ ይባላል - የዘመናት ቁጥር ማለት ነው።

...

በዘመናቱ መካከል አንድ አንድ ጊዜ ክፉ ነገር ቢገጥም፣ መከራም ቢመጣ በተሰጡት ቀናት ማለትም በበዓላት፣ በአጽዋማትና በምኅላ ቀኖች በሱባኤ ወራቶች እግዚአብሔርን ከልብ በመለመን እግዚአብሔር ችግሩን መከራውን እንዲያርቀው  መለመን ነው እንጂ በእግዚአብሔር ላይ መማረርና መሳቀቅ እግዚአብሔርንም መውቀስ አይገባም። እግዚአብሔር ራሱ ባለቤቱ «ንዑ ንትዋቀስ - እኔ እና እናንተ ኑ እንወቃቀስ » ብሎ በኢሳይያስ በተናገረው መሠረት - ይኸውም ለምኑኝ ወደ እኔ ጸልዩ ማለት እንጂ ተከራከሩኝ ማለት አይደለም

...

ሰው እግዚአብሔርን አንተ ታውቃለህ በማለት ሳይሆን በራሱ ፈቃድ የወቀሳ ነገርን በእግዚአብሔር ላይ ሲሰነዝር እግዚአብሔርም መልሱን ይሰጣል፤ ሳይቆጣም ያስረዳል። ለምሳሌ ያህል በባቢሎናዊያን መንደልቶ የተደበደበ ትሩፍ ፈጣሪውን እንዲህ ብሎ አማረረ «ምን ትብከ ተሃሉ ውስተ ሰማይ (ዘእንበሊየ) - ጌታዬ ሆይ አንተ በሰማይ ሆነህ እኔን ለምን አታስበኝም እንዲህ መከራ ስቀበል፣ ስቀጠቀጥ በሰማይ ያሉ መላእክትን ትጠብቃለህን? በመላእክት ላይ የቀን ወራሪ የሌሊት ሰባሪ አለባቸውና እነርሱን እየጠበቅህ ነውን» ብሎ ፈጣሪውን ለመውቀስ ሰንዝሯል። ጌታም መልሶ «ወምንተ እፈቅድ ሃቤከ ውስተ ምድር (ዘእንበሌከ) -  አንተስ በምድር ላይ ሆነህ ምን እየሠራህ እንደሆነ አውቅ የለምን? እኔን ፈጣሪህን አምላክህን ትተህ በምድር ያሉ እንሰሳትን አራዊትን፣ በምድር የሚሳቡትን ፣ በሰማይ ያሉ ፀሐይ ጨረቃ ክዋክብትን እያመለክህ አይደለምን? እንዴት አድርጌ ልስማህ?» ብሎ መልሱን ይሰጠዋል።» ይህ የሊቃውንቱ ጠለቅ ያለ ትርጉም ነው። መዝ. ፸፪(፸፫)፣፳፭

...

ከዚህም ሌላ ዕንባቆምም በጣም ተሳቅቆና ተማርሮ «አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም» ብሎ ተናግሯል። ዕንባቆም ፩፤፪። ስለሆነም በየጊዜው በየዘመኑ መከራ ሲገጥመን እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቀን እኛም ከክፋታችን የምንመልስበትን መንገድ ማሰብ ይገባናል እንጂ መማረር፣ እግዚአብሔርን መውቀስ አይገባንም። በዚህ በዘመኑ ሁከት የሚነሳ፣ መከራ የሚገጥም ቢሆንም ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ተገቢ ነው፤ ሁሉን የሚያርቀው እርሱ ነውና። ለዚህም ከሐዋርያት አብነት እንወስዳለን፦ «በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው። ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምንድን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው። እጅግም ፈሩና እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ይሆን? ተባባሉ። » ማርቆስ ፬፣ ፴፭- ፍጻሜ።

Read More

መልዕክት ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፦ ጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት

መልዕክት ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፦ ጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት

. . . ቅድስት አገራችን ኢትዮጵያም እንዲህ ያለው ውጣ ውረድ በየጊዜው ይፈትናታል። ይኼው ሰሞኑንም የተከሰተው የሰላም ችግርም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። በየጊዜው ከሚነሣ ከእንዲህ ያለው ቀውስ መላቀቅ የሚቻለው ፍጹም ሰላምን የሚያድለውን አምላካችንን በንፁህ ልቡና ሆነን ስንለምነው ነውና "በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ስለከተማይቱ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ" እንዳለ ሁላችንም በአንድነት ሆነን እግዚአብሔር አምላካችን ለአገራችን ለኢትዮጵያ ፍጹም ሰላምን ይሰጥልን ዘንድ በተለይም በዚህ በሱባዔ ወቅት አጥብቀን እንድለምነው አባታዊ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

Read More