ደብረ መንክራት ቅዱስ ገብርኤል ወልደታ ለማርያም፣ ቦስተን

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ፦ መልአከ መንክራት ቀሲስ ነቅዓ ጥበብ የማነ ብርሃን
አድራሻ፦ 162 Goddard Ave, Brookline, MA 02445
ዐበይት የንግሥ በዓላት፦ ቅዱስ ገብርኤል፣ ልደታ ለማርያም
የቤተ ክርስቲያኑ አጭር ታሪክ

የቦስተን ደብረ መንክራት ቅዱስ ገብርኤል ወልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፈቃድ ታኀሣሥ ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከ ሃምሳ ያላነሱ ምእመናን ምእመናት እና ከካህናት ጋር በመሆን ጸሎተ ምህላና እና ኪዳን በማድረስ ተጀመረ።

ታኅሣሥ ፲፩ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ጸሎተ ቡራኩ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ። የዚህ ቤተ ክርስቲያን ዋና አመሠራረት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመቀበል ሥርዓቷንና ቀኖናዋን በማክበር ከካህናት ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን ክርስቲያናዊ ግዴታ በተወጡ ጥቂት ምእመናን ለሁለት ዓመት ያኽል በተደረገ ጥረት ነው። «የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ግን ጥቂቶች» እንዲል በዚህ ወደ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የመመለስ ጥሪ በገለልተኛነት መኖርን የመረጡ በነበሩበት ሲቀሩ መንፈሰ ጠንካራ የሆኑ ጥቂቶች በታላቅ ትጋት ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መመለስን በመምረጥ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዳር ሊደርስላቸው ችሏል። ታኅሣሥ ፲፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ደግሞ የቅዱስ ገብርኤልን ታቦተ ሕግ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ፈቃድና ቡራኬ በማስገባት ቤተ ክርስቲያኑ «ደብረ መንክራት ቅዱስ ገብርኤል ወልደታ ለማርያም» የሚለውን ስያሜ አግኝቷል።