ቅዱስ ፓትርያርኩ ሚኒሶታ ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ቡራኬ ሰጡ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፤ ፓትርያርክ፤ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፤ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በሰሜን ምሥራቅ በደቡብ ምሥራቅ እና በመካከለኛው አሜሪካ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ጋር የሦስት ቀናት ቆይታ ለማድረግ ቅዳሜ ታኅሣሥ ፱/ ፳፻፰ ዓ.ም. የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመጎብኘት ሚኒሶታ ሲገቡ በሚኒያፖሊስ ሴንት ፖል አየር መንገድ ተገኝተው በበርካታ የደብር አስተዳዳሪዎች ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት መዘምራን እና ምእመናን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ከፍተኛ ድምቀት ያለው አቀባበል ተደረገላቸው።

ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ >