ቅዱስ ሲኖዶስ

ቅዱስ ሲኖዶስ

ክርስትና አንድ ጌታ የሚመለክበት በአንዲት ጥምቀት ልጅነት የሚገኝበት በአንድ ተስፋ በአንድነት የሚኖርበት ሃይማኖት ነው፡፡ ይህ እምነት በየጊዜው በዓለም በሚነሱ መጤ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች እንዳይበከል በእርሱም አምነው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚጓዙ አማንያን አንድነታቸው እንዳይፈታ በእግዚአብሔር የተሠራ ጉባዔ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለቤተክርስቲያን ዶግማ ቀኖና ሥርዓትና ትውፊት እንዲሁም አስተዳደር የሚመክሩበት በመንፈስ ቅዱስ የሚቃኝ ጉባዔ ነው፡፡ ይህም «ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት ፓትርያርክ ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚያደርጉት ዓቢይ ጉባዔ ነው፡፡» ተብሎ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የተገለፀው ነው፡፡ /ሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ ፪/፪፡፡

ሙሉውን ያንብቡ

Read More