መሪጌታ ጌታሁንን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለመጨረሻ ጊዜ የላኩት ውሳኔ

መሪጌታ ጌታሁንን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለመጨረሻ ጊዜ የላኩት ውሳኔ

ሕገ እግዚብሔርን እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመተላለፋቸው ምክንያት የተወገዙት መሪጌታ ጌታሁን ጥፋታቸውን አምነው በክርስቶስ ፊት ራሳቸው ዝቅ አድርገው በንስሐ በመመለስ ፋንታ ባሳለፍነው ሳምንትም እንደገና «ቋሚ ሲኖዶስ ውግዘቱን አንስቶልኛል» የሚል አዲስ ደብዳቤ አመጣሁ ማለታቸውን ተከትሎ ውግዘቱን ያስተላለፉትና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ይህንን የመጨረሻ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Read More

በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የሚካሄደውን የአንድነት ጉባኤ አስመልክቶ ከኒውዮርክ ሀገረ ስብከት የተላለፈ መልዕክት

በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የሚካሄደውን የአንድነት ጉባኤ አስመልክቶ ከኒውዮርክ ሀገረ ስብከት የተላለፈ መልዕክት

«አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።»

አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም እንዴትና መቼ እንደሚመጣ ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም የሚያውቅ የለም። የ«ሰላም አለቃ» የተባለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሠረት እና ጉልላት የሆነላት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከንጋት እስከ ሠርክ ባለው ጸሎቷ፣ በማኅሌቷና በቅዳሴዋ ሁሉ ሰላማዊ የሆነውን ወንጌል የምትሰብክ፣ ዓለም የማይሰጠውን ፍጹም ሰላምም ለተከታዮቿ የምታድል ሰላማዊት ቤተ ክርስቲያን ለመሆኗ አምኖ የተከተላትም ሆነ መጠለያ ትሆነው ዘንድ የመረጣት ሕዝብ ሁሉ የመሠከረላት ናት።

Read More

የሐሰት ትርጓሜ የተሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሙሉ ሪፖርት (ሐሰት ውግዘትን አይሸፍንም!)

የሐሰት ትርጓሜ የተሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሙሉ ሪፖርት (ሐሰት ውግዘትን አይሸፍንም!)

በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ በተሰጠው መግለጫ ውስጥ በቁጥር 2 የተጻፈውን

«ከግንቦት ወር 2009 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ ቀን 2010 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፉ ውሳኔዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አማካይነት ቀርበው ምልዓተ ጉባኤው በአፈጻጸማቸው ዙሪያ ከተወያየ በኋላ አስፈላጊውን መመሪያ በመስጠት አጽድቆታል»

ማለቱን ተከትሎ ሚኒያፖሊስ ከተማ የሚገኙትና በፈጸሙት የሃይማኖት እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ምክንያት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የተወገዙት መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ከጭንቀት ብዛት የተነሳ ምእመናንን ያሳምንልኝ ይሆናል? በሚል ዓላማ «በዚህ በቁጥር 2 በቀረበው ሪፖርት ውስጥ የእኔ ውግዘት መነሳት እና ያቋቋምሁት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይም አብሮ ቀርቦ መጽደቁን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የውስጥ አዋቂዎች ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል» በማለት በሃይማኖት ክህደት ላይ ውሸትን በመደራረብ ወደበለጠ ክህደት መሄድ መመረጡ በእጅጉ ያሳዝናል።

ከዚህ በታች ያለው በ 11 ገጽ እና በ 58 ነጥቦች የተተነተነውና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የቀረበው ሙሉ ሪፖርት ላይ ማየት እንደሚቻለው እኒህ ምናባዊያን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻቸው ገለጹልኝ ያሉት የውግዘት መነሳት ጉዳይን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንኩዋንስ ተወያይቶበት ሊያጸድቀው ቀርቶ በሪፖርቱም አልቀረበም። ይህም የሆነው ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መሪጌታው በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተፈትቻለሁ ማለቱን ተከትሎ ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ እንጂ የአስተዳዳር አይደለም በማለት ይግባኝ በማለታቸው ምክያት በዚያው በቋሚ ሲኖዶስ በኩል እንደገና እየታየ ስለሆነ ነው።

ማንበብና መረዳት ለሚችል፣ የሚያገናዝብ አዕምሮ ላለው ሰው ግን እንዲህ ያለው የጎዳና ላይ ማጭበርበር ግለሰቡ በፈጸመው የሃይማኖት እና የሥርዓት ጥሰት ምክያት በደረሰበት ውግዘት በካህናት እና በምእመናን ዘንድ ያዛውን ታማኝነት ለመመለስ ነፋስን የመጎሰም ያኽል ከንቱ ድካም እንደሆነ አያጣውም።

-      አንድ ጊዜ አልተወገዝኩም ማለት፣ በዚህም ለሦስት ዓመታት በሌለው ሥልጣነ ክህነት ምስጢራተ ቤተ ክርስያንን መፈጸም፣

-      መልሶ ደግሞ ከነበረበት ቦታ ሲባረርና የራሱ ቤተ ክርስቲያን መመሠረት ሲፈልግ «ተወግዤ ነበር አሁን ግን ተፈትቻለሁ» ማለት፣

-      ቀጥሎ ደግሞ «አቡነ ዘካርያስ እንዳወገዝኩህ ነው አልተፈታህም» ስላሉኝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መፍትሄ ይሰጠኝ ማለት፣ 

-      ቀጥሎም «አቡነ ዘካርያስ የእኔን ውግዘት መነሳት አስመልክቶ ይግባኝ ያሉት ውድቅ ተደረገልኝ» ብሎ ምናባዊ ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ መዋሸት

-      ይህ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ውግዘት እንደጸና እያለ ብፁዕነታቸው «ከሀገረ ስብከታቸው ተነሱ» የሚለው የሀሰት ወሬ በብሎጎች ሲዘራ ዜናውን በደስት በፌስቡካቸው ማሰራጨት

-      ይህ የዝውውር ወሬ ሀሰት መሆኑ ሲታወቅ ደግሞ «ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካሪያስ ዳግም ተመልሰው ልጆቻቸውን ይባርኩ ዘንድ በጸሎት እና በትጋት ሆነን እንጠብቃለን» የሚል ዜና ማውራት በእውነት

ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ይልቅ በብፁዕነታቸው በተደጋጋሚ እንደተገለጸው የሃይማኖት እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት መፈጸምን አምኖ፣ በሚኒሶታ ምእመናን እና ካህናት ላይ ለዓመታት የተፈጸመውን በደል ተጸጽቶ፣ ውግዘቱን ባስተላለፈው በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የሚሰጠውን ቅጣት ተቀብሎና ፈጽሞ ንስሐ ገብቶ መመለስ እንጂ በየጊዜው ቦታ እና መጠሪያ ስሞችን በመቀያየር፣ የዋህ ምእመናንንም መያዣ አድርጎ ስለ እነርሱ ብላችሁ! እያሉ መጮህ፣ በአንድ በኩል «እሰይ ከሀገረ ስብከታችን ተነሱልን!» እያሉ ሲጮኹ ቆይቶ በሌላ በኩል ደግሞ «ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካሪያስ ዳግም ተመልሰው ልጆቻቸውን ይባርኩ ዘንድ በጸሎት እና በትጋት ሆነን እንጠብቃለን» በሚል የፌዝ ቃል የመንፈስ ሰላምንም ሆነ የምእመናንን አመኔታ ፈጽሞ ማግኘት አያቻልም!

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከኒውዮርክና አካባባቢው ጋር ደርበው ምዕራብ ጎጃም ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከትን እንዲያስተዳድሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከኒውዮርክና አካባባቢው ጋር ደርበው ምዕራብ ጎጃም ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከትን እንዲያስተዳድሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ

የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሰፊና ብዙ ታሪክ ያለው በመሆኑ በዚህች አጭር መልዕክት ሁሉንም መጥቀስ ስለማይቻል ዋናዋውን ብቻ እንጠቅሰዋለን፦

የኒውዮርክን ሀገረ ስብከት የማቋቋም ሥራ የተጀመረው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ 1937 ማለትም ጣልያን ኢትዮጵያን ከወረረበት ጊዜ አንስቶ ነው። ከ 1937 እስከ 1952 ባለው ጊዜም ይህ ይዞታችን በቤተ ክርስቲያን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን በአገር ደረጃ በተለይም በግርማቂ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ጋር በመመካከር ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 አባ ገብረ ኢየሱስ መሸሻ (በኋላ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የሆኑትን አባት) አስፈላጊ የሆኑትን ንዋየ ቅዱሳትና የአጋዕዝት ዓለም ሥላሴን ታቦት ይዘው ወደ Bronx, New York ገብተው አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደረገ። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና ይህም ማለት ከቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ቀጥሎ ከኢትዮጵያ ውጭ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት በሁለተኛ ደረጃ ራሱን የቻለ ጽ/ቤትና መንበረ ጵጵስና ያለው ሆኖ አቅሙ በፈቀደ መጠን ምዕራቡን ክፍለ ዓለም ሲያገለግል የቆየ ነው

ለመጀመሪያ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (በሁዋላ ሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ) የሐረር ሊቀ ጳጳስና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ረዳት ነበሩና በቅዱስነታቸው መልካም ፈቃድ በ 1954 ዓ.ም. ሀገረ ስብከቱን እና ቤተ ክርስቲያኑን ለመጎብኘትና ለማጠናከር መጡ። በዚያን ጊዜ ብፁዕነታቸው 275 የዚህ አገር ተወላጆችን እንዳጠመቁ ታሪክ ይመሰክራል። በኋላም በ 1959 ዓ.ም. ብፁዕነታቸው መጥተው ብዙ ምእመናንን አስተምረውና አጥምቀው ተመልሰዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በጳጳስ ደረጃ ቤተ ክርስቲያኑን እና ሀገረ ስብከቱን ለማቋቋም የተላኩት ታላቁ አባት አባ ገብረ ኢየሱስ አገሩን አውቀውታል ቋንቋውንም በሚገባ አቀላጥፈው ስለሚችሉ ከእርስዎ የተሻለ የለም በማለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተሹመው መጥተው በተለይም በጃማይካና በዚያ አካባቢ የሚገኙ ደሴቶች ብዙ ሕዝብ በማጥመቅ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትንም ተክለዋል።

በ 1962 ዓም ደግሞ አባ ላዕከ ማርያም ማንደፍሮ (በበኋላ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የሆኑት) እያገዟዋቸው በፊት ከነበረው በላይ አንድ ላይ ሆነው ብዙ ሥራ ሠርተዋል። በ 1979ም ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በእድሜ መግፋት ምክንያት ወደ አገራቸው ሲገቡ በእርሳቸው እግር ተተክተው ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል።

ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በኋላ ደግሞ የአሁኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ North America and Canada ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ሀገረ ስብከቱን አስተዳድረዋል። ከዚያም በሁዋላ በምዕራቡ ክፍለ ዓለም የምእመናን እና የአብያተ ክርስቲያናት ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ አስቀድሞ አንድ ሀገረ ስብከት የነበረው የዲሲ፣ የካሊፎርኒያ፣  እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ተብሎ በሦስት አኅጉረ ስብከቶች ሲዋቀር ይህንን ለማሸጋሸግ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲቀየሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ ኒውዮርክ ተመደቡ። ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መልካም ፈቃድና በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ወደ ኒውዮርክ ተመድበው በመምጣት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከትን ላለፉት አሥር ዓመታት እያስተዳደሩ ይገኛሉ።

Read More

የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራውን የሐሰት ምስክርነትን እና የመሪጌታ ጉታሁንን ጉዳይ አስመልክቶ አንዳንዶች ለጠየቁት ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልስ

የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራውን የሐሰት ምስክርነትን እና የመሪጌታ ጉታሁንን ጉዳይ አስመልክቶ አንዳንዶች ለጠየቁት ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልስ

በቋሚ ሲኖዶስ ተነስቶላቸዋል ስለተባለውም ሕጎችን እና ቀኖናዎች ተጠቅሰው ክርክር ተደርጎባቸው ውግዘቱን የሚያነሳ አንዳችም ሕግ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት መካከል አንዳንዶቹ  አልፈረሙበትም።  ምክንያቱም ውግዘቱን አንሰተናል ለሚለው የሚጠቀስ በቂ የሆነ ሕግ የለምና። አንድ ሊቀ ጳጳስ ያወገዘውን ያውም ሐይማኖት እና ቀኖና ሠበር የሆነውን ሌላው ሊቀ ጳጳስ ማንሳት የማይችል መሆኑ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና።

ይህን ጉዳይ የማየት፣ የመመርመር እና ለሁሉም የማሳወቅ ድርሻው የሀገረ ስብከቱ ብቻ ሆኖ ሳለ ራሳቸውን በሊቃውንት ወንበር ላይ ያስቀመጡ እንደ ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ያሉ ሰዎች ግን ሰሚ ተከታይ አለኝ በማለት በምእመን ደረጃ እንኳን የሚታያውቀውን ሕግ በራሱ ሃሳብ ተርጉሞና ይባስ ብሎም «ቋሚ ሲኖዶስ ውግዘቱን ያነሳው አቡነ ዘካርያስ ተወጋዡ ሰው ገዳም ገብቶ ለሦስት ዓመት ጨው የሌለው ቂጣ ካልበላ በስተቀር ይቅር አልለውም ስላሉ ነው» ብሎ ተራ የሐሰት ምስክርነትን ሰጥቷል። ይኸውም የሚያስጠይቀው ነው። ኢትኩን ስምዐ በሀሰት በሀሰት አትመስክር ዘዳ፣5 20 የሚለውን ህግ አፍርሷልና ይህም የቀሲሱን ሥልጣነ ክህነት ሚያሳግድ ይችላል።

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስ የሰጧቸውን ቀኖናዊ ቅጣት ሲጨርሱ የያዙባቸውን ሥልጣነ ክህነት እንደሚያነሱላቸው አስታወቁ፣ የቋሚ ሲኖዶስ የቅርብ ጊዜ አካሄዶች ወደ አንቀጽ 32 እንዳያመራን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰቡ

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስ የሰጧቸውን ቀኖናዊ ቅጣት ሲጨርሱ የያዙባቸውን ሥልጣነ ክህነት እንደሚያነሱላቸው አስታወቁ፣ የቋሚ ሲኖዶስ የቅርብ ጊዜ አካሄዶች ወደ አንቀጽ 32 እንዳያመራን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰቡ

...

ከዚህ ሌላ በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ ራብዕ እንዲሁም በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 32 ከቁጥር 1 እስከ 10 የቅዱስ ፓትርያርክን ተግባር እና ኃላፊነት አስመልክቶ በተደነገገው መሠረት ፓትርያርኩ የሊቀ ጳጳሱን ውግዘት ያነሳል የሚል የለም። ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሦስቱ ማዕረጋተ ክህነት ውስጥ ናቸውና - ጵጵስና፣ ቅስና፣ዲቁና። ፓትርያርክ ከዚህ ውስጥ ነው። ሊቀ ጳጳስ ፓትርያርክ ይባላል። ስለዚህ ከሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር በክህነት አንድ ስለሆነ የሊቀ ጳጳስን ውግዘት እንደሚያነሳ አንዳችም አመላካች ቀኖና የለም።

 

ይህም ቀኖናዊ ሕግ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ላይ እኔም ባለሁበት ወደ ቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ የቀኖና አተረጓጎም ከተሰጠበት በኋላ ይህ ጉዳይ እንደ ሕጉ (ከታች ያለውን ትንታኔ ይመልከቱ) መታየት ያለበት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እንደሆነ ታምኖበት ቋሚ ሲኖዶሱ አመራር በመስጠት ወደ እኔ መርቶታል። በዚህም መሠረት እርስዎም የክህነት እገዳ ይነሣልኝ ጥያቄ ጽሑፍ ወደ እኔ ወደ ሊቀ ጳጳሱ ጽፈዋል።

...

ከዚህም ሌላ በጻፉት ደብዳቤ ላይ «የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳልን» የሚል ቃል ገብቶበታል። እኔ የክርስቶስ ወንጌለ መንግሥት እንዲሰበክና እንዲስፋፋ ሕገ እግዚአብሔርና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደጠበቅ ጥረት የማደርግ እንጅ በማንም ላይ ማዕቀብ የመጣል ሥልጣን የለኝም - በአመፀኞች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚችሉ የዚህ ዓለም መንግሥታት ናቸው።

ስለሆነም በእርስዎ በኩል ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በፈፀሙት ነገር ታግዶ የቆየው የክህነት ሥልጣንዎ በንስሐ ይመለስልዎ ዘንድ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዤ በላክሁልዎት በሌላ ደብዳቤ ላይ የተገለጸውን ቀኖናዊ ቅጣት ፈጽመው ሲጨርሱ የክህነቱ ሥልጣን እግድ የሚነሳ መሆኑን በአክብሮት እገልጽልዎታለሁ።

ከዚህ በተረፈ እግዱን አክብረውና ጠብቀው ለቆዩ ምእመናን ምስጋና ይገባቸዋል።

የቀኖና ቡራኬው ያልተፈጸመለት ቤተ ክርስቲያንም በሐዲስ መንፈስ በቅብዓ ሜሮን ታትሞ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚደረግ መሆኑን ጨምሬ አሳስባለሁ።

Read More

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የያዙትን ሥልጣነ ክህነት የማንሳት ሥልጣን እንደሌለው አምኖ የቦስተኑ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስን ጉዳይ ወደ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መራው

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የያዙትን ሥልጣነ ክህነት የማንሳት ሥልጣን እንደሌለው አምኖ የቦስተኑ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስን ጉዳይ ወደ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መራው

-       በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተያዘባቸውን ሥልጣነ ክህነት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ለማስመለስ የሄዱትን የቦስተኑ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስን ጉዳይ መርምሮ መወሰን ሥልጣኑ እንዳልሆነ የተረዳው ቋሚ ሲኖዶስ ጉዳዩን ወደ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መራው።

-       ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከሳምንታት በፊት ለሚኒያፖሊሱ መሪጌታ ጌታሁን «ሥልጣነ ክህነትህን መልሼልሃለሁ» ያለው ቋሚ ሲኖዶስ ይህን የማድረግ ሥልጣን እንደሌለው አስገንዝበው የመሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት አሁንም እንደጸና ነው ማለታቸው አይዘነጋም። ያን ጊዜም ያሉት ይህንን ነበር ዛሬም የተወሰነው ይህ ነው - ቋሚ ሲኖዶስ አንድ ሊቀ ጳጳስ የያዘውን ሥልጣነ ክህነት የማንሳት ሥልጣን ሕገ ሲኖዶስ አልሰጠውም- ከዚህ በፊትም ተደርጎም አያውቅም!

Read More

ቋሚ ሲኖዶስ «አንስቻለሁ» ያለው የሚኒያፖሊሱ መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት እንደፀና ነው ፣ የአቡነ ዳንኤል ተደጋጋሚ ጣልቃ ገብነት እና ትምህርትም የሚያስወግዝ ነው /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ቋሚ ሲኖዶስ «አንስቻለሁ» ያለው የሚኒያፖሊሱ መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት እንደፀና ነው ፣ የአቡነ ዳንኤል ተደጋጋሚ ጣልቃ ገብነት እና ትምህርትም የሚያስወግዝ ነው /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ይሁን እንጂ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 28 ከቁጥር 1 -12 በተዘረዘረው መሠረት አንድ ሊቀ ጳጳስ ያሳለፈውን ውግዘት ቋሚ ሲኖዶስ ማንሳት እንደሚችል የሚያመላክት ሥልጣን የለውም፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ከማስፈጸም በስተቀር። ስለዚህ ውግዘቱ አቡነ ዳንኤልን ጨምሮ የጸና ስለሆነ በሚኒያፖሊስ ከተማ አዲስ ተከፈተ እየተባለ በሚነገረው ቤተ ክርስቲያን ማንኛውም የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዳይሳተፉ! ይህን ማድረግ ከክህደቱ ጋር መተባበር ነውና - እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፦ «ለመስተካህድ ብእሲ እም ከመ ምዕረ ወካዕበ ገሠፅኮ ወአበየ ህድጎ ወአምሮ ከመ አላዊ ውዕቱ ዘከማሁ ያስህት ወያጌጊ ወይረክብ ኩነኔ» ቲቶ 3 1-12

Read More

«ከዚህ በተረፈ በእኔ በኩል የሐይማኖት ጉዳይ ነውና ውግዘቱ እንደፀና መሆኑ እንዲታወቅልኝ በትህትና አሳስባለሁ» /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

«ከዚህ በተረፈ በእኔ በኩል የሐይማኖት ጉዳይ ነውና ውግዘቱ እንደፀና መሆኑ እንዲታወቅልኝ በትህትና አሳስባለሁ» /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ብፁዕ ወቅዱስ ሆይ

ይህ በአስቸኳይ እና በድንገት የተላለፈው በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈው ውሳኔ እንደገና እንዲታይ ቢደረግ መሪጌታ ጌታሁንም ሰፋ ያለ የንስሐ ጊዜ ተሰጥቶአቸው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ገብተው እንዲያገለግሉ ቢደረግ የተፈቀደላቸው ቤተ ክርስቲያንም እንደ ሕጉ በሀገረ ስብከቱ በኩል ተጠንቶ እንዲፈቀድላቸው ቢሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ይግባኝ ስለጠየቅሁ ይግባኙ ተፈቅዶ በምልአተ ጉባኤው እንዲታይልኝ።

Read More

በቀድሞው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የነበሩትን ለማናገር የላክሁት ልዑክ የለም፤ እነርሱን አስመልክቶም የተለወጠ ነገር የለም /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

በቀድሞው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የነበሩትን ለማናገር የላክሁት ልዑክ የለም፤ እነርሱን አስመልክቶም የተለወጠ ነገር የለም /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ቤተ ክርስቲያን የምሕረት ቤት ናት። ከእናት ቤተ ክርስቲያን ተለይቶ መንፈሳዊ ሕይወት መምራት ከንቱ ድካም እንደሆነ ምዕመናን ተረድተው መነሳሳታቸው መልካም ነው። መሪ ነኝ የሚለው ካህን ትክክለኛ መንገድ ነው ስላላቸው ብቻ የተከተሉትን አካሄድ ዛሬ ላይ ሲገመግሙት ስህተት መሆኑን ተረድተው ወደ እውነት ለመመለስ ማሰባቸው አስተዋይነት ነው። ወደ እውነት በሚደረግ ጉዞ ግን ጥፋት ነው ብለው ያመኑበትን ተግባር አሁንም ደግመው እየፈጸሙ ሳይሆን በቁርጥ ሃሳብ እና በፍፁም ልብ መመለስን ይጠይቃል። በአንድ በኩል ውግዘቴን አሥነሳለሁ፣ ሥላጣነ ክህነቴን አስመልሳለሁ እየተባለ በሌላ በኩል በዚያው የለኝም ተወስዶብኛል በተባለው ክህነት መስቀል ይዞ እያሳለሙ፣ እየቀደሱ ፣ እያጠመቁ ለሦስት ዓመት ኖሮ አሁንም በዚያው ማዕርግ ነኝ የሚል መሪ አሁንም ተከታዮቹን እንደ ዋስትና አስይዞ ለራስ ጥቅም መደራደሪያ ለማድረግ እንጂ የልብ መጸጸት እና መመለስ እንደሌለው ያሳያል።

ጥፋትን አምኖ እና ተጸጽቶ የመጣን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷን መመሪያ በማድረግ መጸጸቱትና እና መመለሱን መዝና እንደሥርዓቱ ቀጥታ ወደ ቤቷ ትቀበለዋለች። ሆኖም ግን አሁንም በዚያው በቀደመው ኅሊና እና ማንነት ላይ ቆሞ ምሕረት እንዲሁ ይደረግልኝ ማለት ራስን ከማሞኘት ያለፈ  አይሆንም።

Read More

የሊቃውንት ጉባኤ «ወልደ አብ» የተባለውን መጽሐፍ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ ሰጠ፤ ጸሐፊው ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ!

የሊቃውንት ጉባኤ «ወልደ አብ» የተባለውን መጽሐፍ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ ሰጠ፤ ጸሐፊው ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ!

የሊቃውንት ጉባኤ «ወልደ አብ» የተባለውን መጽሐፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ያግደው ዘንድ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መጠየቃቸውንና ማውገዛቸውን ተከትሎ ካጠና በሁዋላ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የሐሰት፣ የኑፋቄ እና የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ ሰጠ፤ ጸሐፊው ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ሌሎቹን ይዞ እንዳይጠፋ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ!

Read More

ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ በመግባት የመሠረት ድንጋይ እንዳያስቀምጡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ታገዱ

ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ በመግባት የመሠረት ድንጋይ እንዳያስቀምጡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ታገዱ

ክርስቶሳዊት እና ሐዋርያዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያናችን በሐዋርያት መንበር የተቀመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፈጽሞ ሊያደርጉት በማይገባ መልኩ ሕገ እግዚአብሔርን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በድጋሚ በመተላለፍ በሀገረ ስብከትዎ በድሬዳዋ ብቻ እንጂ በሌላ ቦታ ያለ ፈቃድ ሊፈጽሙት የማይገባዎትን ተግባር እፈጽማለሁ ማለትዎ ሕገ እግዚአብሔርን መሻር ስለሆነ ይህንን ከተወገዙ ካህናት ጋር ሆነው እፈጽመዋለሁ ያሉት የአዲስ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥን አንሥተን እና አግደን በፊርማዎ ባጸደቁትና ከዚህ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ላይ በተወሰነውና «ይህ ደብዳቤ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ሕጉ ተጠብቆ እንዲሠራ ሆኖ ከሕጉ ከቀኖናው እና ከሥርዓቱ ውጭ ተፈጽሞ ቢገኝ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ በተቀመጠው ሕግ (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 38 ተራ ቁጥር 3 እና ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ከቁጥር 156- 161) መሠረት የሚፈጸም መሆኑን እናስታውቃለን» ባለው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያስተላልፍበት ዘንድ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከተጨማሪ ማስረጃዎች ጋር ማስተላለፋችንንም ጨምረን እንገልጽልዎታለን።

Read More

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሀገረ ስብከት ጣልቃ ገብነትን አስመልክቶ ውሳኔ አስተላለፈ

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በሀገረ ስብከት ጣልቃ ገብነትን አስመልክቶ ውሳኔ አስተላለፈ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት የሚፈጸመውን ጣልቃ ገብነት አስመልክቶ በስፋት ከተወያየ በኋላ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

ሊቃነ ጳጳሳት ያለ ሀገረ ስብከታቸው በመግባት አዲስ ታቦተ ሕግ መስጠት፣ የዲቁን እና የቅስና ማዕርግ መስጠት፣ መዳኘት፣ የአዲስ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ማስቀመጥ እና የመሳሰሉት ዐበይት ተግባራት መፈጸም አይችሉም ሲል አስቀድሞ የነበረውን ሕግ በማጽናት ውሳኔ አስተላልፏል።

ከሕጉና ከቀኖናው ውጪ ተፈጽሞ ቢገኝ ግን በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 38 በተራ ቁጥር 3 በተደነገገውና በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ከቁጥር 156-161 በተደነገገው መሠረት ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ተፈጻሚ እንደሚሆንበት ደንግጓል።

 

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ዘመን መለወጫን እና የሀገረ ስብከቱ ዌብ ሳይት መጀመርን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ዘመን መለወጫን እና የሀገረ ስብከቱ ዌብ ሳይት መጀመርን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

የተከበራችሁ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪም የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ሁላችሁ! የዘመናት ጌታ የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አደረሳችሁ እያልኹ ይኽንን የከበረ አባታዊ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።

...

በዚህ የዘመን መቁጠሪያ አጽዋማት፣ በዓላት፣ አውራኅ፣ ዓመታት እና ቀኖች እነዚህ ሁሉ የሚውሉበት አጠናቅቀው ያውቁበታል። በዚህም የምኅላ ቀናት፣ የጸሎት ቀናት፣ የበዓላት ቀናት ብለው ለይተው ያውቃሉ፤ እግዚአብሔርንም ይማልዱበታል። ይህ በአጠቃላይ ትርጉሙ ባሕረ ሃሳብ ይባላል - የዘመናት ቁጥር ማለት ነው።

...

በዘመናቱ መካከል አንድ አንድ ጊዜ ክፉ ነገር ቢገጥም፣ መከራም ቢመጣ በተሰጡት ቀናት ማለትም በበዓላት፣ በአጽዋማትና በምኅላ ቀኖች በሱባኤ ወራቶች እግዚአብሔርን ከልብ በመለመን እግዚአብሔር ችግሩን መከራውን እንዲያርቀው  መለመን ነው እንጂ በእግዚአብሔር ላይ መማረርና መሳቀቅ እግዚአብሔርንም መውቀስ አይገባም። እግዚአብሔር ራሱ ባለቤቱ «ንዑ ንትዋቀስ - እኔ እና እናንተ ኑ እንወቃቀስ » ብሎ በኢሳይያስ በተናገረው መሠረት - ይኸውም ለምኑኝ ወደ እኔ ጸልዩ ማለት እንጂ ተከራከሩኝ ማለት አይደለም

...

ሰው እግዚአብሔርን አንተ ታውቃለህ በማለት ሳይሆን በራሱ ፈቃድ የወቀሳ ነገርን በእግዚአብሔር ላይ ሲሰነዝር እግዚአብሔርም መልሱን ይሰጣል፤ ሳይቆጣም ያስረዳል። ለምሳሌ ያህል በባቢሎናዊያን መንደልቶ የተደበደበ ትሩፍ ፈጣሪውን እንዲህ ብሎ አማረረ «ምን ትብከ ተሃሉ ውስተ ሰማይ (ዘእንበሊየ) - ጌታዬ ሆይ አንተ በሰማይ ሆነህ እኔን ለምን አታስበኝም እንዲህ መከራ ስቀበል፣ ስቀጠቀጥ በሰማይ ያሉ መላእክትን ትጠብቃለህን? በመላእክት ላይ የቀን ወራሪ የሌሊት ሰባሪ አለባቸውና እነርሱን እየጠበቅህ ነውን» ብሎ ፈጣሪውን ለመውቀስ ሰንዝሯል። ጌታም መልሶ «ወምንተ እፈቅድ ሃቤከ ውስተ ምድር (ዘእንበሌከ) -  አንተስ በምድር ላይ ሆነህ ምን እየሠራህ እንደሆነ አውቅ የለምን? እኔን ፈጣሪህን አምላክህን ትተህ በምድር ያሉ እንሰሳትን አራዊትን፣ በምድር የሚሳቡትን ፣ በሰማይ ያሉ ፀሐይ ጨረቃ ክዋክብትን እያመለክህ አይደለምን? እንዴት አድርጌ ልስማህ?» ብሎ መልሱን ይሰጠዋል።» ይህ የሊቃውንቱ ጠለቅ ያለ ትርጉም ነው። መዝ. ፸፪(፸፫)፣፳፭

 

...

ከዚህም ሌላ ዕንባቆምም በጣም ተሳቅቆና ተማርሮ «አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም» ብሎ ተናግሯል። ዕንባቆም ፩፤፪። ስለሆነም በየጊዜው በየዘመኑ መከራ ሲገጥመን እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቀን እኛም ከክፋታችን የምንመልስበትን መንገድ ማሰብ ይገባናል እንጂ መማረር፣ እግዚአብሔርን መውቀስ አይገባንም። በዚህ በዘመኑ ሁከት የሚነሳ፣ መከራ የሚገጥም ቢሆንም ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ተገቢ ነው፤ ሁሉን የሚያርቀው እርሱ ነውና። ለዚህም ከሐዋርያት አብነት እንወስዳለን፦ «በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው። ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱት፥ ሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ። ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ። እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምንድን ነው? እንዴትስ እምነት የላችሁም? አላቸው። እጅግም ፈሩና እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ይሆን? ተባባሉ። » ማርቆስ ፬፣ ፴፭- ፍጻሜ።

 

Read More

ጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት

 ጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት

... ቅድስት አገራችን ኢትዮጵያም እንዲህ ያለው ውጣ ውረድ በየጊዜው ይፈትናታል። ይኼው ሰሞኑንም የተከሰተው የሰላም ችግርም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲጠፋ ምክንያት ሆኗል። በየጊዜው ከሚነሣ ከእንዲህ ያለው ቀውስ መላቀቅ የሚቻለው ፍጹም ሰላምን የሚያድለውን አምላካችንን በንፁህ ልቡና ሆነን ስንለምነው ነውና "በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ስለከተማይቱ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ" እንዳለ ሁላችንም በአንድነት ሆነን እግዚአብሔር አምላካችን ለአገራችን ለኢትዮጵያ ፍጹም ሰላምን ይሰጥልን ዘንድ በተለይም በዚህ በሱባዔ ወቅት አጥብቀን እንድለምነው አባታዊ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

Read More