ሊቀ ትጉኃን መሪጌታ ጌታሁን መሠረትኩት ያሉት ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሕጋዊ እውቅና እንደሌለው ስለማሳወቅ

ሊቀ ትጉኃን መሪጌታ ጌታሁን መሠረትኩት ያሉት ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሕጋዊ እውቅና እንደሌለው ስለማሳወቅ

Download PDF Document

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይከበር ዘንድ ሊሟሉ የሚገባቸውን መስፈርቶችን ለባለ ጉዳዩና ይህንንም ለጠየቀኝ ሁሉ ባስረዳም፣ ባለጉዳዩም እኒህ ሁኔታዎች እንዲሟሉ እና ስህቱም እንዲታረም እንደሚፈልጉ ከገለጹልኝ በኋላ ለሀገረ ስብከቱ የላኩት ደብዳቤ ግን ድፍረት የተሞላበት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን መተላለፉን ያመነ፣ ወደፊትም ለመታረም የተዘጋጀ ሰው የሚጽፈው ደብዳቤ ሳይሆን ሽቅብ ወደ ላይ ትዕዛዝን የሚያዝዝ ሆኖ ማገኘታችን በጣም አሳዝኖናል።

 

እርስዎም መስከረም 5 ቀን 2011 በጻፉት ደብዳቤ ላይም፦  

1.     መሠረትኩት ስላሉት ቤተ ክርስቲያን ሲናገሩ «በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መመሥረቱ ለብፁነትዎ የተሰወረ አይደለም» ብለዋል። ይህ ንስሐ የገቡበትን በደል መልሶ የመሥራት ያክል ታላቅ ድፍረት ነው። ከላይ በጠቀስኩት የሕገ ቤተ ክርስቲያን መተላለፍ እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ምክንያት ሥልጣነ ክህነትዎ ተይዞብዎት ቆይተው «ቋሚ ሲኖዶስ ሥልጣነ ክህነቴን መለሰልኝ» የሚል ደብዳቤ ከአንድም ሁለት ጊዜ ቢያመጡም ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ፍጹም ስሕተት እና ውግዙትንም የማያስነሳ በመሆኑ ከካህናት ጋር ሳይጨመሩ በውግዘት ተለይተው ለብቻዎት ቆይተው እንደነበረ ሁሉም የሚያውቀው እውነታ ነው። በስተመጨረሻ ግን ይህንን ተረድተውና የባልንጀራዎችዎን ምክር ሰምተው እንደ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መመሪያ መሠረት ውግዘቱን ካስተላለፈው ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ንስሐ ገብተው ክህነትዎ ሊመለስልዎት እንደሚገባ የተነገረዎትን ሰምተው ውግዘቱን ላስተላለፍኩት ለእኔ ለክፍሉ ሊቀ ጳጳስ በጻፉት የይቅርታ ደብዳቤ መሠረት ንስሐ ገብተው ክህነትዎን ስለመለስኹልዎት በቀደመው ክብር ሆነው ከካህናት ወንድሞችዎት ጋር ለመጨመር በቅተዋል።

 

ይህ ትምህርት ሊሆንዎት ሲገባ አሁንም ተመልሰው «በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ መመሥረቱ ለብፁነትዎ የተሰወረ አይደለም» ሲሉ መናገርዎት በጥፋትዎ መጸጸትዎትን እና ከስህተትዎም መማርዎትን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። እርስዎ እንደሚሉት ይህንን ማድረግ የሌላ የቤተ ክርስቲያን አካል ሥልጣን እና ኃላፊነት ቢሆን ኖሮ መጀመሪያ ጀምረው ከአንድም ሁለት ጊዜ «ክህነቴን ቋሚ ሲኖዶስ መለሰልኝ» እንዳሉ በዚያው በጸኑ ነበር። አሁንም ቢሆን በአንድ ሀገረ ስብከት ሥር በየትኛው ቦታ፣ ምን ምን ሁኔታዎች ሲሟሉ፣ የካህኑንም ማንነት መርምሮና፣ ለአካባቢው ምእመናን አገልግሎት የሚሰጡ በቂ አብያተ ክርስቲያናት አለመኖራቸውን አገናዝቦና ሌሎችንም ሁኔታዎች አጥንቶ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሠረት ማቀድ፣ መፍቀድ የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ እንጂ የማንም ሥልጣን እና ኃላፊነት አይደለም። «ቋሚ ሲኖዶስ» የሚለውን ስም ለምእመናኑ ደግሞ ደጋግሞ በመናገር በምእመናን ዘንድ ሕጋዊነት ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ በማስጠብቅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ፣ ለኅሊናም እረፍትን የሚሰጥ ሥራን መሥራትን ቢመርጡ በተሻለ ነበር። አሁንም ደግሜ የማሳስብዎት ይህንኑ ነው።

 

2.    ክህነትዎን ሳያስመልሱ በሌለዎት ሥልጣነ ክህነት መሠረትኩት ያሉትን ቤተ ክርስቲያን እንደ ሕጋዊ ቤተ ክርስቲያን በመቁጠር «በብፁዕነትዎ ሀገረ ስብከት ስር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲታወቅልን እና ካሉትም አብያተ ክርስቲያናት ጋር በአንድነት መገልገል እንድንችል በብፁዕነትዎ በኩል እንዲያሳውቁልን» ሲሉ መጻፍዎት እውቀት ማጣት ይሁን ወይም ድፍረት መለየት ተቸግረናል። ሁለቱም ግን ቤተ ክርስቲያንን አስተዳድራለሁ ከሚል ካህን የማይጠበቅ በሚዛንም ሲቀመጥ የሚቀልል ተግባር ነው።

 

3.    የቋሚ ሲኖዶስ ሥልጣን እና ኃላፊነት ምን ድረስ እንደሆነ የቤተ ክርስቲያኗን ሕግና ሥርዓት ጠንቅቆ የተረዳ፣ የተጻፈውንም ሕግ ለማመሳከር የወደደ ሁሉ የሚውቀው ነው። በአንድ ሊቀ ጳጳስ ሀገረ ስብከት ገብቶ ቤተ ክርስቲያን የመክፈትም ሆነ የሊቀ ጳጳሱን የትኛውን የሥራ ድርሻ እና ሥልጣን መጋፋት አይችልም። በዚህ ላይም ደግሞ ይባስ ብሎ ውክልና ተሰጥቶኛል በማለት ሰሜን አሜሪካ ድረስ መጥተው ይህንን ቤተ ክርስቲያን ያለ ሀገረ ስብከታቸው መሠረትኩት የሚሉትን የድሬዳዋው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዳንኤል በጌታችን በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በተናገሩት የክህደት ትምህርት ምክንያት በሙሉ ማስረጃ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቤ እየተመረመረ የሚገኝ ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ለእርስዎ የተሰወረ አይደለም፤ ምክንያቱም ለሦስት ዓመታት ሲያስተዳድሩት ከነበረውና ከወራት በፊት በምእመናኑና በአስተዳደር ጽ/ቤቱ ውሳኔ መሠረት እንዲለቁ በተደረጉት ቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት እርስዎ በተቀመጡበት የተነገረ፣ ቪዲዮው በዓለም የተሰራጨ፣ ሊቃውንትና ምእመናን ያዘኑበት ትልቅ የክህደት ትምህርት ነው። እንዲህ ያለውን ክህደት በተናገሩ አባት ተመሠረተልኝ መባሉ በጥፋት ላይ ሌላ ድርብ ጥፋት ያደርገዋል።

ስለሆነም የተመለሰልዎትን ሥልጣነ ክህነት አስመልክቶ ማንም ጥያቄ ሊያነሳብዎት እንደማይገባ ሁሉም እንዲያውቀው እያሳሰብን፤ ሆኖም ግን መሠረትኩት ያሉት ቤተ ክርስቲያን ግን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የተላለፈ እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በጣሰ መልኩ የተመሠረተ ሰለሆነ ሀገረ ስብከታችን ከሕጋዊ ቤተ ክርስቲያን ምድብ የማይቆጥረው ስለሆነ በአካባቢው የሚገኙ ካህናት፣ ዲያቆናት እና የሰንበት ትምሕርት ቤት ወጣቶች በዚያ ስፍራ በአገልግሎት መተባበር እንደማይችሉ በአጽንዖት እናሳስባለን። በስልክ ንግራችን ወቅት በግልጽ ያስረዳኹዎትን አሟልተውና ይህንንም ገልጸው በደብዳቤ በሚጠይቁበት ወቅት የሚገባው ሥርዓት ተፈጽሞ ሕጋዊ ቤተ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ጉዳዩን ወደፊት ልናየው የምንችለው ይሆናል።

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር ለመካተት በመወሰናቸው ደስታቸው ገለጹ፣ የሊቀ ትጉሃን መሪጌታ ጌታሁን መኮንንን ጨምሮ የሁሉንም ካህናት ተይዞ የነበረውን ሥልጣነ ክንነታቸውን መለሱ!

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር ለመካተት በመወሰናቸው ደስታቸው ገለጹ፣ የሊቀ ትጉሃን መሪጌታ ጌታሁን መኮንንን ጨምሮ የሁሉንም ካህናት ተይዞ የነበረውን ሥልጣነ ክንነታቸውን መለሱ!


ይህ ልዩነት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተከሰተ ቢሆንም በሚኒያፖሊስ ከተማ የሆነው ግን በብዙዎች ዘንድ የተሰማ ስለነበረ ይህ ሲኖዶሳዊ አስተዳደር ልዩነትና ፈተናዎቹ በሚነሣባቸው ቦታዎች ሁሉ እንደማጣቀሻ ሆኖ ሲነገር ቆይቷል። በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በትጋት በምታገለግሉ ልጆቻችን መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመዳኘት፣ እንደ አባትነታችን እና እንደ ክፍሉ ሊቀ ጳጳስነቴም በምክርና በተግሳጽ ቀና የሆነውን የሐይማኖት መንገድ ለማሳየት በማሰብ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መጋቢት ፳፯ እና ፳፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በተገኘንበት ዕለት ያጋጠመን ሁኔታ ግን ከዚያ ቀን ቀደም ብሎ ያላጋጠመኝና አንድ ኦርቶዶክሳዊ ልጅ ለመንፈስ አባቱ ሊያሳየው ያማይገባው በመሆኑ እኔንም በእጅጉ ያሳዘነ ነበር። እናንተም ብትሆኑ በወቅቱ በስሜት በመገፋፋት ብታደርጉትም ጊዜው ሲያልፍ ብዙም የምትደሰቱበት እንደማይሆን በሁላችንም የታወቀ ነበር።

ይህችንም ቀን ተከትሎ ችግሮች እየተባባሱ መጥተው ካህናት በአቋም ተለያዩ፣ ምእመናንም ለሁለት ተከፈሉ። በኃላፊነት ወንበር እንደተቀመጠ ማንኛውም ኃላፊ፣ ይልቁንም ደግሞ በሃይማኖታዊ ኃላፊነት የቅዱስ ሲኖዶስን ውክልና ይዞ እንደተቀመጠ ሊቀ ጳጳስነቴም ውክልና የሰጠኝን አካል መመሪያ ማስፈጸም መንፈሳዊ ግዴታዬ ነውና የተፈጠረው ልዩነት ያስከተለውን ችግር ለመቅረፍ ሲባል የተቀበልኩት ኃላፊነት የሚያስገድደኝን ሁሉ አድርጌአለሁ።

ቢቻልስ ኖሮ «በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ» ሐዋ. ፪፣፵፩ እንዳለ የዚያን ቀንም ሆነ በሌሎች ቀናትም ተመላልሼ በአንዲቱ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምዕመናኑ ቁጥር በሦስት ሺህ ጨምሮ አስተምሬ በመንፈስ ባጎለመስኳችሁ፣ ቀድሼም ባቆረብኳችሁ በወደድኹ ነበር። የዘመኑ ፈተና ግን ይህ እንዲሆን አላደረገምና በሆነው ሁሉ እናዝናለን። «እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ይህን አልጽፍም» ፩ኛ ቆሮ ፬፣፲፬ እንዲል ይህንን ጦማር የምጽፍላችሁ በዚያ ቀን ስለተፈጠረው እያሰባችሁ ከእንግዲህ እንዳታዝኑ በፍጹም ልብ ይቅር ማለቴን አሳውቃችሁ ዘንድ እንጅ ያንን በማድረጋችሁ ዛሬ ላሳፍራችሁ አይደለም።

ከዚያች ቀን በኋላ በተፈጠረው ልዩነት ለዓመታት በአንድነት ይኖር የነበሩ ምእመናንን በአካሄድ ተለያይተው አንዱ ወደዚህ አንዱ ወደዚያ ሆነ። ይህንንም ተከትሎ የእናንተው ወንድሞች እና እህቶቻችሁ ከዚህ መንጋ ያልሆኑ ሌሎችንም ጨምረው ርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴን ካቴድራልን መሠረቱ። «እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው» ዘፍጥ. ፶፣፳ - እንዲል ይህ በመሆኑ ከመጀመሪያው በረት ያልነበሩ ሌሎች ወገኖች ወደ በረቱ ለማምጣት ምክንያት ሆነ፣ በሁለታችሁም ብርታት በርካታ መምህራነ ወንጌል መጥተው የክርስቶስ ወንጌል ተሰበከ። የልዩነት ጊዜውን ዛሬ እግዚአብሔር አሳልፎልን በአንድ ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳዳደር ሥር ሆናችሁ በጋራ የምታለሙትን ሰፊ እርሻ ሰጣችሁ። ለወደፊቱም በጎ ኅሊና ያላቸው ሠራተኞች ሆናችሁ ቤተ ክርስቲያኖቻችሁን አሁን ካሉበት ወደላቀ ደረጃ ማሳደግ ድርሻው የእናንተ ነው ፦ ያጠፋን ካህን የገሰጽሁት፣ የተሳሳተንም አካል በመጽሐፍ ላይ በሠፈረ ሕግ የሞገትኹት ይህች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓቷ ተጠብቆ ይኖር ዘንድ ነውና።  

Read More

ያለፈውን ልዩነታችንን አስወግደን በጋራ ለመሥራት የቀረበ ጥሪ

ያለፈውን ልዩነታችንን አስወግደን በጋራ ለመሥራት የቀረበ ጥሪ

ላለፉት በርካታ ዓመታት በመካከላችን ተገንብቶ ስናስታምመውና ሲያሳምመን በነበነረበው ሲኖዶሳዊ የአስተዳደር ልዩነት ምክንያት የመጣብንን መለያየት እግዚአብሔር የመረጣት ቀን ደርሳ ወደ አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር ለመምጣት በመቻላችን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን። በዚህም አስተዳደራዊ ልዩነት ሳቢያ በሦስት ጎራ ተከፍለን ስደተኛ፣ የእናት ቤተ ክርስቲያን እና ገለልተኛ በማለት በመለያየታችን የተነሣ አባቶች ሆድና ጀርባ ሆነዋል፣ ቤተሰብም ተለያይቷል። በአንድ ሃይማኖት ሆነን፣ በአንድ ሥርዓተ አምልኮ እያመለክን፣ በአንድ ቋንቋ አገልግሎት እየሰጠን ነገር ግን ተለያይተን ተኳርፈናል፣ ተካሰናል፣ ፍርድ ቤት ቆመናል፣ ገበናችንን ለባዕዳን፣ ገንዘባችንን ለጠበቆች፣ ጉልበታችንን ለብክነት አውለናል። ይህ ሁሉ ኪሣራ በልዩነት ምክንያት ያገኘን ኪሣራ ነው።

ዛሬ ግን «ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር» ነውና ቤተ ክርስቲያናችን ወደ ቀደመ ሲኖዶሳዊ አንድነቷ ተመልሳ ሁላችንንም በአንድነት ለመሰብሰብ የሰላም አዋጅ አውጃ ልጆቷን እየሰበሰበች ትገኛለች። ይህ እኛ በዘመናችን ያመጣንባት ችግር ጠባሳው እንዲሽርና መጪው ትውልድም ልዕልናዋን እና ክብሯን እንጂ እኛ ያደረስንባትን ድቀት እንዳያስታውስ ያለፈውን ልዩነታችንን ረስተን በሰላም እና በአንድነት እንሠራ ዘንድ ሀገረ ስብከታችን ለሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በጋራ የመስራት ጥሪውን ያስተላልፋል። በአብያተ ክርስቲያናት መካከል የተጀመረው የጎንዮሽ አንድነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያሳሰብን ሀገረ ስብከታችንም ከዚህ በፊት የነበረውን ልዩነት አስወግዶ በመወያየትና በመመካከር ለበለጠ ሥራ እንድንሣሣ ለሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጥሪውን ያስተላልፋል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ሲኖዶሳዊ ዕርቀ ሰላሙ ላይ በተገለጸውና የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ባሳሰቡት መሠረት ከነገ እሑድ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፩፲ ዓ.ም. ጀምሮ  በሀገረ ስብከታችን በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ በቅዳሴ፣ በጸሎትና በማንኛውም አገልግሎት ጊዜ የኹለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮቻችን ስም እንዲነሣ እያሳሰብን፣ ሁላችሁም በፍቅር አገልግሎት ሆናችሁ ወደዚህ አንድነትና ሕብረት ያልመጡ ካሉ ይመጡ ዘንድ እንድትተጉ ጨምረን እናሳስባለን።

Read More

መሪጌታ ጌታሁንን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለመጨረሻ ጊዜ የላኩት ውሳኔ

መሪጌታ ጌታሁንን አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለመጨረሻ ጊዜ የላኩት ውሳኔ

ሕገ እግዚብሔርን እና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመተላለፋቸው ምክንያት የተወገዙት መሪጌታ ጌታሁን ጥፋታቸውን አምነው በክርስቶስ ፊት ራሳቸው ዝቅ አድርገው በንስሐ በመመለስ ፋንታ ባሳለፍነው ሳምንትም እንደገና «ቋሚ ሲኖዶስ ውግዘቱን አንስቶልኛል» የሚል አዲስ ደብዳቤ አመጣሁ ማለታቸውን ተከትሎ ውግዘቱን ያስተላለፉትና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሳስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ይህንን የመጨረሻ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Read More

በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የሚካሄደውን የአንድነት ጉባኤ አስመልክቶ ከኒውዮርክ ሀገረ ስብከት የተላለፈ መልዕክት

በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የሚካሄደውን የአንድነት ጉባኤ አስመልክቶ ከኒውዮርክ ሀገረ ስብከት የተላለፈ መልዕክት

«አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል። በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።»

አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም እንዴትና መቼ እንደሚመጣ ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም የሚያውቅ የለም። የ«ሰላም አለቃ» የተባለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሠረት እና ጉልላት የሆነላት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከንጋት እስከ ሠርክ ባለው ጸሎቷ፣ በማኅሌቷና በቅዳሴዋ ሁሉ ሰላማዊ የሆነውን ወንጌል የምትሰብክ፣ ዓለም የማይሰጠውን ፍጹም ሰላምም ለተከታዮቿ የምታድል ሰላማዊት ቤተ ክርስቲያን ለመሆኗ አምኖ የተከተላትም ሆነ መጠለያ ትሆነው ዘንድ የመረጣት ሕዝብ ሁሉ የመሠከረላት ናት።

Read More

የሐሰት ትርጓሜ የተሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሙሉ ሪፖርት (ሐሰት ውግዘትን አይሸፍንም!)

የሐሰት ትርጓሜ የተሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሙሉ ሪፖርት (ሐሰት ውግዘትን አይሸፍንም!)

በግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ በተሰጠው መግለጫ ውስጥ በቁጥር 2 የተጻፈውን

«ከግንቦት ወር 2009 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ ቀን 2010 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፉ ውሳኔዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አማካይነት ቀርበው ምልዓተ ጉባኤው በአፈጻጸማቸው ዙሪያ ከተወያየ በኋላ አስፈላጊውን መመሪያ በመስጠት አጽድቆታል»

ማለቱን ተከትሎ ሚኒያፖሊስ ከተማ የሚገኙትና በፈጸሙት የሃይማኖት እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ምክንያት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የተወገዙት መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ከጭንቀት ብዛት የተነሳ ምእመናንን ያሳምንልኝ ይሆናል? በሚል ዓላማ «በዚህ በቁጥር 2 በቀረበው ሪፖርት ውስጥ የእኔ ውግዘት መነሳት እና ያቋቋምሁት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይም አብሮ ቀርቦ መጽደቁን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የውስጥ አዋቂዎች ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል» በማለት በሃይማኖት ክህደት ላይ ውሸትን በመደራረብ ወደበለጠ ክህደት መሄድ መመረጡ በእጅጉ ያሳዝናል።

ከዚህ በታች ያለው በ 11 ገጽ እና በ 58 ነጥቦች የተተነተነውና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የቀረበው ሙሉ ሪፖርት ላይ ማየት እንደሚቻለው እኒህ ምናባዊያን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻቸው ገለጹልኝ ያሉት የውግዘት መነሳት ጉዳይን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንኩዋንስ ተወያይቶበት ሊያጸድቀው ቀርቶ በሪፖርቱም አልቀረበም። ይህም የሆነው ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መሪጌታው በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተፈትቻለሁ ማለቱን ተከትሎ ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ እንጂ የአስተዳዳር አይደለም በማለት ይግባኝ በማለታቸው ምክያት በዚያው በቋሚ ሲኖዶስ በኩል እንደገና እየታየ ስለሆነ ነው።

ማንበብና መረዳት ለሚችል፣ የሚያገናዝብ አዕምሮ ላለው ሰው ግን እንዲህ ያለው የጎዳና ላይ ማጭበርበር ግለሰቡ በፈጸመው የሃይማኖት እና የሥርዓት ጥሰት ምክያት በደረሰበት ውግዘት በካህናት እና በምእመናን ዘንድ ያዛውን ታማኝነት ለመመለስ ነፋስን የመጎሰም ያኽል ከንቱ ድካም እንደሆነ አያጣውም።

-      አንድ ጊዜ አልተወገዝኩም ማለት፣ በዚህም ለሦስት ዓመታት በሌለው ሥልጣነ ክህነት ምስጢራተ ቤተ ክርስያንን መፈጸም፣

-      መልሶ ደግሞ ከነበረበት ቦታ ሲባረርና የራሱ ቤተ ክርስቲያን መመሠረት ሲፈልግ «ተወግዤ ነበር አሁን ግን ተፈትቻለሁ» ማለት፣

-      ቀጥሎ ደግሞ «አቡነ ዘካርያስ እንዳወገዝኩህ ነው አልተፈታህም» ስላሉኝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መፍትሄ ይሰጠኝ ማለት፣ 

-      ቀጥሎም «አቡነ ዘካርያስ የእኔን ውግዘት መነሳት አስመልክቶ ይግባኝ ያሉት ውድቅ ተደረገልኝ» ብሎ ምናባዊ ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ መዋሸት

-      ይህ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ውግዘት እንደጸና እያለ ብፁዕነታቸው «ከሀገረ ስብከታቸው ተነሱ» የሚለው የሀሰት ወሬ በብሎጎች ሲዘራ ዜናውን በደስት በፌስቡካቸው ማሰራጨት

-      ይህ የዝውውር ወሬ ሀሰት መሆኑ ሲታወቅ ደግሞ «ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካሪያስ ዳግም ተመልሰው ልጆቻቸውን ይባርኩ ዘንድ በጸሎት እና በትጋት ሆነን እንጠብቃለን» የሚል ዜና ማውራት በእውነት

ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ይልቅ በብፁዕነታቸው በተደጋጋሚ እንደተገለጸው የሃይማኖት እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት መፈጸምን አምኖ፣ በሚኒሶታ ምእመናን እና ካህናት ላይ ለዓመታት የተፈጸመውን በደል ተጸጽቶ፣ ውግዘቱን ባስተላለፈው በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የሚሰጠውን ቅጣት ተቀብሎና ፈጽሞ ንስሐ ገብቶ መመለስ እንጂ በየጊዜው ቦታ እና መጠሪያ ስሞችን በመቀያየር፣ የዋህ ምእመናንንም መያዣ አድርጎ ስለ እነርሱ ብላችሁ! እያሉ መጮህ፣ በአንድ በኩል «እሰይ ከሀገረ ስብከታችን ተነሱልን!» እያሉ ሲጮኹ ቆይቶ በሌላ በኩል ደግሞ «ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካሪያስ ዳግም ተመልሰው ልጆቻቸውን ይባርኩ ዘንድ በጸሎት እና በትጋት ሆነን እንጠብቃለን» በሚል የፌዝ ቃል የመንፈስ ሰላምንም ሆነ የምእመናንን አመኔታ ፈጽሞ ማግኘት አያቻልም!

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከኒውዮርክና አካባባቢው ጋር ደርበው ምዕራብ ጎጃም ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከትን እንዲያስተዳድሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከኒውዮርክና አካባባቢው ጋር ደርበው ምዕራብ ጎጃም ፍኖተ ሰላም ሀገረ ስብከትን እንዲያስተዳድሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ

የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሰፊና ብዙ ታሪክ ያለው በመሆኑ በዚህች አጭር መልዕክት ሁሉንም መጥቀስ ስለማይቻል ዋናዋውን ብቻ እንጠቅሰዋለን፦

የኒውዮርክን ሀገረ ስብከት የማቋቋም ሥራ የተጀመረው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ 1937 ማለትም ጣልያን ኢትዮጵያን ከወረረበት ጊዜ አንስቶ ነው። ከ 1937 እስከ 1952 ባለው ጊዜም ይህ ይዞታችን በቤተ ክርስቲያን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን በአገር ደረጃ በተለይም በግርማቂ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ጋር በመመካከር ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 አባ ገብረ ኢየሱስ መሸሻ (በኋላ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የሆኑትን አባት) አስፈላጊ የሆኑትን ንዋየ ቅዱሳትና የአጋዕዝት ዓለም ሥላሴን ታቦት ይዘው ወደ Bronx, New York ገብተው አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደረገ። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና ይህም ማለት ከቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ቀጥሎ ከኢትዮጵያ ውጭ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት በሁለተኛ ደረጃ ራሱን የቻለ ጽ/ቤትና መንበረ ጵጵስና ያለው ሆኖ አቅሙ በፈቀደ መጠን ምዕራቡን ክፍለ ዓለም ሲያገለግል የቆየ ነው

ለመጀመሪያ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ (በሁዋላ ሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ) የሐረር ሊቀ ጳጳስና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ረዳት ነበሩና በቅዱስነታቸው መልካም ፈቃድ በ 1954 ዓ.ም. ሀገረ ስብከቱን እና ቤተ ክርስቲያኑን ለመጎብኘትና ለማጠናከር መጡ። በዚያን ጊዜ ብፁዕነታቸው 275 የዚህ አገር ተወላጆችን እንዳጠመቁ ታሪክ ይመሰክራል። በኋላም በ 1959 ዓ.ም. ብፁዕነታቸው መጥተው ብዙ ምእመናንን አስተምረውና አጥምቀው ተመልሰዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በጳጳስ ደረጃ ቤተ ክርስቲያኑን እና ሀገረ ስብከቱን ለማቋቋም የተላኩት ታላቁ አባት አባ ገብረ ኢየሱስ አገሩን አውቀውታል ቋንቋውንም በሚገባ አቀላጥፈው ስለሚችሉ ከእርስዎ የተሻለ የለም በማለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ተሹመው መጥተው በተለይም በጃማይካና በዚያ አካባቢ የሚገኙ ደሴቶች ብዙ ሕዝብ በማጥመቅ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትንም ተክለዋል።

በ 1962 ዓም ደግሞ አባ ላዕከ ማርያም ማንደፍሮ (በበኋላ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የሆኑት) እያገዟዋቸው በፊት ከነበረው በላይ አንድ ላይ ሆነው ብዙ ሥራ ሠርተዋል። በ 1979ም ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በእድሜ መግፋት ምክንያት ወደ አገራቸው ሲገቡ በእርሳቸው እግር ተተክተው ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል።

ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በኋላ ደግሞ የአሁኑ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ North America and Canada ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ሀገረ ስብከቱን አስተዳድረዋል። ከዚያም በሁዋላ በምዕራቡ ክፍለ ዓለም የምእመናን እና የአብያተ ክርስቲያናት ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ አስቀድሞ አንድ ሀገረ ስብከት የነበረው የዲሲ፣ የካሊፎርኒያ፣  እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ተብሎ በሦስት አኅጉረ ስብከቶች ሲዋቀር ይህንን ለማሸጋሸግ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲቀየሩ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ ኒውዮርክ ተመደቡ። ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መልካም ፈቃድና በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ወደ ኒውዮርክ ተመድበው በመምጣት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከትን ላለፉት አሥር ዓመታት እያስተዳደሩ ይገኛሉ።

Read More

የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራውን የሐሰት ምስክርነትን እና የመሪጌታ ጉታሁንን ጉዳይ አስመልክቶ አንዳንዶች ለጠየቁት ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልስ

የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራውን የሐሰት ምስክርነትን እና የመሪጌታ ጉታሁንን ጉዳይ አስመልክቶ አንዳንዶች ለጠየቁት ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልስ

በቋሚ ሲኖዶስ ተነስቶላቸዋል ስለተባለውም ሕጎችን እና ቀኖናዎች ተጠቅሰው ክርክር ተደርጎባቸው ውግዘቱን የሚያነሳ አንዳችም ሕግ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት መካከል አንዳንዶቹ  አልፈረሙበትም።  ምክንያቱም ውግዘቱን አንሰተናል ለሚለው የሚጠቀስ በቂ የሆነ ሕግ የለምና። አንድ ሊቀ ጳጳስ ያወገዘውን ያውም ሐይማኖት እና ቀኖና ሠበር የሆነውን ሌላው ሊቀ ጳጳስ ማንሳት የማይችል መሆኑ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና።

ይህን ጉዳይ የማየት፣ የመመርመር እና ለሁሉም የማሳወቅ ድርሻው የሀገረ ስብከቱ ብቻ ሆኖ ሳለ ራሳቸውን በሊቃውንት ወንበር ላይ ያስቀመጡ እንደ ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ያሉ ሰዎች ግን ሰሚ ተከታይ አለኝ በማለት በምእመን ደረጃ እንኳን የሚታያውቀውን ሕግ በራሱ ሃሳብ ተርጉሞና ይባስ ብሎም «ቋሚ ሲኖዶስ ውግዘቱን ያነሳው አቡነ ዘካርያስ ተወጋዡ ሰው ገዳም ገብቶ ለሦስት ዓመት ጨው የሌለው ቂጣ ካልበላ በስተቀር ይቅር አልለውም ስላሉ ነው» ብሎ ተራ የሐሰት ምስክርነትን ሰጥቷል። ይኸውም የሚያስጠይቀው ነው። ኢትኩን ስምዐ በሀሰት በሀሰት አትመስክር ዘዳ፣5 20 የሚለውን ህግ አፍርሷልና ይህም የቀሲሱን ሥልጣነ ክህነት ሚያሳግድ ይችላል።

Read More

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስ የሰጧቸውን ቀኖናዊ ቅጣት ሲጨርሱ የያዙባቸውን ሥልጣነ ክህነት እንደሚያነሱላቸው አስታወቁ፣ የቋሚ ሲኖዶስ የቅርብ ጊዜ አካሄዶች ወደ አንቀጽ 32 እንዳያመራን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰቡ

ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ለሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስ የሰጧቸውን ቀኖናዊ ቅጣት ሲጨርሱ የያዙባቸውን ሥልጣነ ክህነት እንደሚያነሱላቸው አስታወቁ፣ የቋሚ ሲኖዶስ የቅርብ ጊዜ አካሄዶች ወደ አንቀጽ 32 እንዳያመራን ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳሰቡ

...

ከዚህ ሌላ በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ ራብዕ እንዲሁም በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 32 ከቁጥር 1 እስከ 10 የቅዱስ ፓትርያርክን ተግባር እና ኃላፊነት አስመልክቶ በተደነገገው መሠረት ፓትርያርኩ የሊቀ ጳጳሱን ውግዘት ያነሳል የሚል የለም። ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሦስቱ ማዕረጋተ ክህነት ውስጥ ናቸውና - ጵጵስና፣ ቅስና፣ዲቁና። ፓትርያርክ ከዚህ ውስጥ ነው። ሊቀ ጳጳስ ፓትርያርክ ይባላል። ስለዚህ ከሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር በክህነት አንድ ስለሆነ የሊቀ ጳጳስን ውግዘት እንደሚያነሳ አንዳችም አመላካች ቀኖና የለም።

 

ይህም ቀኖናዊ ሕግ የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ላይ እኔም ባለሁበት ወደ ቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ የቀኖና አተረጓጎም ከተሰጠበት በኋላ ይህ ጉዳይ እንደ ሕጉ (ከታች ያለውን ትንታኔ ይመልከቱ) መታየት ያለበት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እንደሆነ ታምኖበት ቋሚ ሲኖዶሱ አመራር በመስጠት ወደ እኔ መርቶታል። በዚህም መሠረት እርስዎም የክህነት እገዳ ይነሣልኝ ጥያቄ ጽሑፍ ወደ እኔ ወደ ሊቀ ጳጳሱ ጽፈዋል።

...

ከዚህም ሌላ በጻፉት ደብዳቤ ላይ «የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳልን» የሚል ቃል ገብቶበታል። እኔ የክርስቶስ ወንጌለ መንግሥት እንዲሰበክና እንዲስፋፋ ሕገ እግዚአብሔርና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደጠበቅ ጥረት የማደርግ እንጅ በማንም ላይ ማዕቀብ የመጣል ሥልጣን የለኝም - በአመፀኞች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚችሉ የዚህ ዓለም መንግሥታት ናቸው።

ስለሆነም በእርስዎ በኩል ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በፈፀሙት ነገር ታግዶ የቆየው የክህነት ሥልጣንዎ በንስሐ ይመለስልዎ ዘንድ ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዤ በላክሁልዎት በሌላ ደብዳቤ ላይ የተገለጸውን ቀኖናዊ ቅጣት ፈጽመው ሲጨርሱ የክህነቱ ሥልጣን እግድ የሚነሳ መሆኑን በአክብሮት እገልጽልዎታለሁ።

ከዚህ በተረፈ እግዱን አክብረውና ጠብቀው ለቆዩ ምእመናን ምስጋና ይገባቸዋል።

የቀኖና ቡራኬው ያልተፈጸመለት ቤተ ክርስቲያንም በሐዲስ መንፈስ በቅብዓ ሜሮን ታትሞ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚደረግ መሆኑን ጨምሬ አሳስባለሁ።

Read More

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የያዙትን ሥልጣነ ክህነት የማንሳት ሥልጣን እንደሌለው አምኖ የቦስተኑ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስን ጉዳይ ወደ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መራው

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የያዙትን ሥልጣነ ክህነት የማንሳት ሥልጣን እንደሌለው አምኖ የቦስተኑ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስን ጉዳይ ወደ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መራው

-       በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተያዘባቸውን ሥልጣነ ክህነት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ለማስመለስ የሄዱትን የቦስተኑ ሊቀ ጉባኤ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስን ጉዳይ መርምሮ መወሰን ሥልጣኑ እንዳልሆነ የተረዳው ቋሚ ሲኖዶስ ጉዳዩን ወደ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መራው።

-       ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከሳምንታት በፊት ለሚኒያፖሊሱ መሪጌታ ጌታሁን «ሥልጣነ ክህነትህን መልሼልሃለሁ» ያለው ቋሚ ሲኖዶስ ይህን የማድረግ ሥልጣን እንደሌለው አስገንዝበው የመሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት አሁንም እንደጸና ነው ማለታቸው አይዘነጋም። ያን ጊዜም ያሉት ይህንን ነበር ዛሬም የተወሰነው ይህ ነው - ቋሚ ሲኖዶስ አንድ ሊቀ ጳጳስ የያዘውን ሥልጣነ ክህነት የማንሳት ሥልጣን ሕገ ሲኖዶስ አልሰጠውም- ከዚህ በፊትም ተደርጎም አያውቅም!

Read More

ቋሚ ሲኖዶስ «አንስቻለሁ» ያለው የሚኒያፖሊሱ መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት እንደፀና ነው ፣ የአቡነ ዳንኤል ተደጋጋሚ ጣልቃ ገብነት እና ትምህርትም የሚያስወግዝ ነው /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ቋሚ ሲኖዶስ «አንስቻለሁ» ያለው የሚኒያፖሊሱ መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት እንደፀና ነው ፣ የአቡነ ዳንኤል ተደጋጋሚ ጣልቃ ገብነት እና ትምህርትም የሚያስወግዝ ነው /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ይሁን እንጂ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 28 ከቁጥር 1 -12 በተዘረዘረው መሠረት አንድ ሊቀ ጳጳስ ያሳለፈውን ውግዘት ቋሚ ሲኖዶስ ማንሳት እንደሚችል የሚያመላክት ሥልጣን የለውም፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ከማስፈጸም በስተቀር። ስለዚህ ውግዘቱ አቡነ ዳንኤልን ጨምሮ የጸና ስለሆነ በሚኒያፖሊስ ከተማ አዲስ ተከፈተ እየተባለ በሚነገረው ቤተ ክርስቲያን ማንኛውም የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዳይሳተፉ! ይህን ማድረግ ከክህደቱ ጋር መተባበር ነውና - እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፦ «ለመስተካህድ ብእሲ እም ከመ ምዕረ ወካዕበ ገሠፅኮ ወአበየ ህድጎ ወአምሮ ከመ አላዊ ውዕቱ ዘከማሁ ያስህት ወያጌጊ ወይረክብ ኩነኔ» ቲቶ 3 1-12

Read More

«ከዚህ በተረፈ በእኔ በኩል የሐይማኖት ጉዳይ ነውና ውግዘቱ እንደፀና መሆኑ እንዲታወቅልኝ በትህትና አሳስባለሁ» /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

«ከዚህ በተረፈ በእኔ በኩል የሐይማኖት ጉዳይ ነውና ውግዘቱ እንደፀና መሆኑ እንዲታወቅልኝ በትህትና አሳስባለሁ» /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ብፁዕ ወቅዱስ ሆይ

ይህ በአስቸኳይ እና በድንገት የተላለፈው በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈው ውሳኔ እንደገና እንዲታይ ቢደረግ መሪጌታ ጌታሁንም ሰፋ ያለ የንስሐ ጊዜ ተሰጥቶአቸው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን ገብተው እንዲያገለግሉ ቢደረግ የተፈቀደላቸው ቤተ ክርስቲያንም እንደ ሕጉ በሀገረ ስብከቱ በኩል ተጠንቶ እንዲፈቀድላቸው ቢሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ይግባኝ ስለጠየቅሁ ይግባኙ ተፈቅዶ በምልአተ ጉባኤው እንዲታይልኝ።

Read More

በቀድሞው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የነበሩትን ለማናገር የላክሁት ልዑክ የለም፤ እነርሱን አስመልክቶም የተለወጠ ነገር የለም /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

በቀድሞው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የነበሩትን ለማናገር የላክሁት ልዑክ የለም፤ እነርሱን አስመልክቶም የተለወጠ ነገር የለም /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ቤተ ክርስቲያን የምሕረት ቤት ናት። ከእናት ቤተ ክርስቲያን ተለይቶ መንፈሳዊ ሕይወት መምራት ከንቱ ድካም እንደሆነ ምዕመናን ተረድተው መነሳሳታቸው መልካም ነው። መሪ ነኝ የሚለው ካህን ትክክለኛ መንገድ ነው ስላላቸው ብቻ የተከተሉትን አካሄድ ዛሬ ላይ ሲገመግሙት ስህተት መሆኑን ተረድተው ወደ እውነት ለመመለስ ማሰባቸው አስተዋይነት ነው። ወደ እውነት በሚደረግ ጉዞ ግን ጥፋት ነው ብለው ያመኑበትን ተግባር አሁንም ደግመው እየፈጸሙ ሳይሆን በቁርጥ ሃሳብ እና በፍፁም ልብ መመለስን ይጠይቃል። በአንድ በኩል ውግዘቴን አሥነሳለሁ፣ ሥላጣነ ክህነቴን አስመልሳለሁ እየተባለ በሌላ በኩል በዚያው የለኝም ተወስዶብኛል በተባለው ክህነት መስቀል ይዞ እያሳለሙ፣ እየቀደሱ ፣ እያጠመቁ ለሦስት ዓመት ኖሮ አሁንም በዚያው ማዕርግ ነኝ የሚል መሪ አሁንም ተከታዮቹን እንደ ዋስትና አስይዞ ለራስ ጥቅም መደራደሪያ ለማድረግ እንጂ የልብ መጸጸት እና መመለስ እንደሌለው ያሳያል።

ጥፋትን አምኖ እና ተጸጽቶ የመጣን ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷን መመሪያ በማድረግ መጸጸቱትና እና መመለሱን መዝና እንደሥርዓቱ ቀጥታ ወደ ቤቷ ትቀበለዋለች። ሆኖም ግን አሁንም በዚያው በቀደመው ኅሊና እና ማንነት ላይ ቆሞ ምሕረት እንዲሁ ይደረግልኝ ማለት ራስን ከማሞኘት ያለፈ  አይሆንም።

Read More

የሊቃውንት ጉባኤ «ወልደ አብ» የተባለውን መጽሐፍ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ ሰጠ፤ ጸሐፊው ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ!

የሊቃውንት ጉባኤ «ወልደ አብ» የተባለውን መጽሐፍ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ ሰጠ፤ ጸሐፊው ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ!

የሊቃውንት ጉባኤ «ወልደ አብ» የተባለውን መጽሐፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ያግደው ዘንድ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መጠየቃቸውንና ማውገዛቸውን ተከትሎ ካጠና በሁዋላ «የቅብዐትና የጸጋ የክህደት ትምህርትን የማስፋፋት ዓላማ ያለው የሐሰት፣ የኑፋቄ እና የክህደት መጽሐፍ ነው» ሲል ውሳኔ ሰጠ፤ ጸሐፊው ገብረ መድኅን እንዳለውም «መጽሐፉን አውግዞ ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ ሌሎቹን ይዞ እንዳይጠፋ ከቤተ ክርስቲያን እንዲለይ ይደረግ» ሲል የውሳኔ ሃሳብ ሰጠ!

Read More

ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ በመግባት የመሠረት ድንጋይ እንዳያስቀምጡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ታገዱ

ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ በመግባት የመሠረት ድንጋይ እንዳያስቀምጡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ታገዱ

ክርስቶሳዊት እና ሐዋርያዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያናችን በሐዋርያት መንበር የተቀመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፈጽሞ ሊያደርጉት በማይገባ መልኩ ሕገ እግዚአብሔርን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በድጋሚ በመተላለፍ በሀገረ ስብከትዎ በድሬዳዋ ብቻ እንጂ በሌላ ቦታ ያለ ፈቃድ ሊፈጽሙት የማይገባዎትን ተግባር እፈጽማለሁ ማለትዎ ሕገ እግዚአብሔርን መሻር ስለሆነ ይህንን ከተወገዙ ካህናት ጋር ሆነው እፈጽመዋለሁ ያሉት የአዲስ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥን አንሥተን እና አግደን በፊርማዎ ባጸደቁትና ከዚህ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ላይ በተወሰነውና «ይህ ደብዳቤ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ሕጉ ተጠብቆ እንዲሠራ ሆኖ ከሕጉ ከቀኖናው እና ከሥርዓቱ ውጭ ተፈጽሞ ቢገኝ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ በተቀመጠው ሕግ (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 38 ተራ ቁጥር 3 እና ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ከቁጥር 156- 161) መሠረት የሚፈጸም መሆኑን እናስታውቃለን» ባለው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያስተላልፍበት ዘንድ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከተጨማሪ ማስረጃዎች ጋር ማስተላለፋችንንም ጨምረን እንገልጽልዎታለን።

Read More