ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ያለ ሀገረ ስብከታቸው ጣልቃ በመግባት የመሠረት ድንጋይ እንዳያስቀምጡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ታገዱ


ክርስቶሳዊት እና ሐዋርያዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያናችን በሐዋርያት መንበር የተቀመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፈጽሞ ሊያደርጉት በማይገባ መልኩ ሕገ እግዚአብሔርን እና የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በድጋሚ በመተላለፍ በሀገረ ስብከትዎ በድሬዳዋ ብቻ እንጂ በሌላ ቦታ ያለ ፈቃድ ሊፈጽሙት የማይገባዎትን ተግባር እፈጽማለሁ ማለትዎ ሕገ እግዚአብሔርን መሻር ስለሆነ ይህንን ከተወገዙ ካህናት ጋር ሆነው እፈጽመዋለሁ ያሉት የአዲስ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ማስቀመጥን አንሥተን እና አግደን በፊርማዎ ባጸደቁትና ከዚህ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ላይ በተወሰነውና «ይህ ደብዳቤ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ሕጉ ተጠብቆ እንዲሠራ ሆኖ ከሕጉ ከቀኖናው እና ከሥርዓቱ ውጭ ተፈጽሞ ቢገኝ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ በተቀመጠው ሕግ (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 38 ተራ ቁጥር 3 እና ፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 1 ከቁጥር 156- 161) መሠረት የሚፈጸም መሆኑን እናስታውቃለን» ባለው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ያስተላልፍበት ዘንድ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከተጨማሪ ማስረጃዎች ጋር ማስተላለፋችንንም ጨምረን እንገልጽልዎታለን።

READ MORE PDF