የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራውን የሐሰት ምስክርነትን እና የመሪጌታ ጉታሁንን ጉዳይ አስመልክቶ አንዳንዶች ለጠየቁት ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መልስ

ጉዳዩ፦ የመሪጌታ ጌታሁን መኮንን ውግዘት መነሳት አለመነሳትን አስመልክቶ አንዳንዶች ላቀረባችሁት ጥያቄ መልስ መስጠትን ይመለከታል 

ይህንን ጉዳይ አስመልክተን ቀደም ብለን የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዎችን ጠቅሰን እንደጻፍንላችሁ ሁላችሁም የምታውቁት ነው። በቋሚ ሲኖዶስ ተነስቶላቸዋል ስለተባለውም ሕጎችን እና ቀኖናዎች ተጠቅሰው ክርክር ተደርጎባቸው ውግዘቱን የሚያነሳ አንዳችም ሕግ አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት መካከል አንዳንዶቹ  አልፈረሙበትም።  ምክንያቱም ውግዘቱን አንሰተናል ለሚለው የሚጠቀስ በቂ የሆነ ሕግ የለምና። አንድ ሊቀ ጳጳስ ያወገዘውን ያውም ሐይማኖት እና ቀኖና ሠበር የሆነውን ሌላው ሊቀ ጳጳስ ማንሳት የማይችል መሆኑ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና።

ይህን ጉዳይ የማየት፣ የመመርመር እና ለሁሉም የማሳወቅ ድርሻው የሀገረ ስብከቱ ብቻ ሆኖ ሳለ ራሳቸውን በሊቃውንት ወንበር ላይ ያስቀመጡ እንደ ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው ያሉ ሰዎች ግን ሰሚ ተከታይ አለኝ በማለት በምእመን ደረጃ እንኳን የሚታያውቀውን ሕግ በራሱ ሃሳብ ተርጉሞና ይባስ ብሎም «ቋሚ ሲኖዶስ ውግዘቱን ያነሳው አቡነ ዘካርያስ ተወጋዡ ሰው ገዳም ገብቶ ለሦስት ዓመት ጨው የሌለው ቂጣ ካልበላ በስተቀር ይቅር አልለውም ስላሉ ነው» ብሎ ተራ የሐሰት ምስክርነትን ሰጥቷል። ይኸውም የሚያስጠይቀው ነው። ኢትኩን ስምዐ በሀሰት በሀሰት አትመስክር ዘዳ፣5 20 የሚለውን ህግ አፍርሷልና ይህም የቀሲሱን ሥልጣነ ክህነት ሚያሳግድ ይችላል።

ስለሆነም ውግዘቱ በምንም አይነት ያልተነሳ በመሆኑ ከላይ በስም የተጠቀሱት ሰው ጥንታዊትና እና ሐዋርያዊት ሥርዓት ጠብቃ በምትገኘው በኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ባሉ አብያተ ክርስቲያን በማንኛውም ክብረ በዓልና ዓመት በዓል እንዲጋበዙና እንዲያገለግሉ የማይፈቀድ መሆኑን አውቃችሁ ይህንን መመሪያም ምእመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እንዲያውቁት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
 

dejeneAndGetahun.jpg
DEJENEPOST.PNG