የሐሰት ትርጓሜ የተሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሙሉ ሪፖርት (ሐሰት ውግዘትን አይሸፍንም!)

-      የተያያዘውን በ 11 ገጾች እና በ 58 ነጥቦች የተተነተነው የቅዱስ ሲኖዶስ ሪፖርት 

ሙሉውን የቅዱስ ሲኖዶስ ሪፖርት  [download PDF] በመጫን ማግኘት ይቻላል።

ግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ በተሰጠው መግለጫ ውስጥ በቁጥር 2 የተጻፈውን

«ከግንቦት ወር 2009 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ ቀን 2010 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤና በቋሚ ሲኖዶስ የተላለፉ ውሳኔዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አማካይነት ቀርበው ምልዓተ ጉባኤው በአፈጻጸማቸው ዙሪያ ከተወያየ በላ አስፈላጊውን መመሪያ በመስጠት አጽድቆታል»

ማለቱን ተከትሎ ሚኒያፖሊስ ከተማ የሚገኙትና በፈጸሙት የሃይማኖት እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ምክንያት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የተወገዙት መሪጌታ ጌታሁን መኮንን ከጭንቀት ብዛት የተነሳ ምእመናንን ያሳምንልኝ ይሆናል? በሚል ዓላማ «በዚህ በቁጥር 2 በቀረበው ሪፖርት ውስጥ የእኔ ውግዘት መነሳት እና ያቋቋምሁት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይም አብሮ ቀርቦ መጽደቁን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው የውስጥ አዋቂዎች ምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል» በማለት በሃይማኖት ክህደት ላይ ውሸትን በመደራረብ ወደበለጠ ክህደት መሄድ መመረጡ በእጅጉ ያሳዝናል።

ከዚህ በታች ያለው በ 11 ገጽ እና በ 58 ነጥቦች የተተነተነውና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የቀረበው ሙሉ ሪፖርት ላይ ማየት እንደሚቻለው እኒህ ምናባዊያን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻቸው ገለጹልኝ ያሉት የውግዘት መነሳት ጉዳይን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንኩዋንስ ተወያይቶበት ሊያጸድቀው ቀርቶ በሪፖርቱም አልቀረበም። ይህም የሆነው ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ መሪጌታው በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተፈትቻለሁ ማለቱን ተከትሎ ጉዳዩ የሃይማኖት ጉዳይ እንጂ የአስተዳዳር አይደለም በማለት ይግባኝ በማለታቸው ምክያት በዚያው በቋሚ ሲኖዶስ በኩል እንደገና እየታየ ስለሆነ ነው።

ማንበብና መረዳት ለሚችል፣ የሚያገናዝብ አዕምሮ ላለው ሰው ግን እንዲህ ያለው የጎዳና ላይ ማጭበርበር ግለሰቡ በፈጸመው የሃይማኖት እና የሥርዓት ጥሰት ምክያት በደረሰበት ውግዘት በካህናት እና በምእመናን ዘንድ ያዛውን ታማኝነት ለመመለስ ነፋስን የመጎሰም ያኽል ከንቱ ድካም እንደሆነ አያጣውም።

-      አንድ ጊዜ አልተወገዝኩም ማለት፣ በዚህም ለሦስት ዓመታት በሌለው ሥልጣነ ክህነት ምስጢራተ ቤተ ክርስያንን መፈጸም፣

-      መልሶ ደግሞ ከነበረበት ቦታ ሲባረርና የራሱ ቤተ ክርስቲያን መመሠረት ሲፈልግ «ተወግዤ ነበር አሁን ግን ተፈትቻለሁ» ማለት፣

-      ቀጥሎ ደግሞ «አቡነ ዘካርያስ እንዳወገዝኩህ ነው አልተፈታህም» ስላሉኝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መፍትሄ ይሰጠኝ ማለት፣ 

-      ቀጥሎም «አቡነ ዘካርያስ የእኔን ውግዘት መነሳት አስመልክቶ ይግባኝ ያሉት ውድቅ ተደረገልኝ» ብሎ ምናባዊ ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ መዋሸት

-      ይህ የብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ውግዘት እንደጸና እያለ ብፁዕነታቸው «ከሀገረ ስብከታቸው ተነሱ» የሚለው የሀሰት ወሬ በብሎጎች ሲዘራ ዜናውን በደስት በፌስቡካቸው ማሰራጨት

-      ይህ የዝውውር ወሬ ሀሰት መሆኑ ሲታወቅ ደግሞ «ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካሪያስ ዳግም ተመልሰው ልጆቻቸውን ይባርኩ ዘንድ በጸሎት እና በትጋት ሆነን እንጠብቃለን» የሚል ዜና ማውራት በእውነት

ከዚህ ሁሉ ጭንቀት ይልቅ በብፁዕነታቸው በተደጋጋሚ እንደተገለጸው የሃይማኖት እና የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት መፈጸምን አምኖ፣ በሚኒሶታ ምእመናን እና ካህናት ላይ ለዓመታት የተፈጸመውን በደል ተጸጽቶ፣ ውግዘቱን ባስተላለፈው በክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የሚሰጠውን ቅጣት ተቀብሎና ፈጽሞ ንስሐ ገብቶ መመለስ እንጂ በየጊዜው ቦታ እና መጠሪያ ስሞችን በመቀያየር፣ የዋህ ምእመናንንም መያዣ አድርጎ ስለ እነርሱ ብላችሁ! እያሉ መጮህ፣ በአንድ በኩል «እሰይ ከሀገረ ስብከታችን ተነሱልን!» እያሉ ሲጮኹ ቆይቶ በሌላ በኩል ደግሞ «ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካሪያስ ዳግም ተመልሰው ልጆቻቸውን ይባርኩ ዘንድ በጸሎት እና በትጋት ሆነን እንጠብቃለን» በሚል የፌዝ ቃል የመንፈስ ሰላምንም ሆነ የምእመናንን አመኔታ ፈጽሞ ማግኘት አያቻልም!

 

FALSE.PNG
LetterFromHG.jpg