በቀድሞው ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የነበሩትን ለማናገር የላክሁት ልዑክ የለም፤ እነርሱን አስመልክቶም የተለወጠ ነገር የለም /ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ/

ቤተ ክርስቲያን የምሕረት ቤት ናት። ከእናት ቤተ ክርስቲያን ተለይቶ መንፈሳዊ ሕይወት መምራት ከንቱ ድካም እንደሆነ ምዕመናን ተረድተው መነሳሳታቸው መልካም ነው። መሪ ነኝ የሚለው ካህን ትክክለኛ መንገድ ነው ስላላቸው ብቻ የተከተሉትን አካሄድ ዛሬ ላይ ሲገመግሙት ስህተት መሆኑን ተረድተው ወደ እውነት ለመመለስ ማሰባቸው አስተዋይነት ነው። ወደ እውነት በሚደረግ ጉዞ ግን ጥፋት ነው ብለው ያመኑበትን ተግባር አሁንም ደግመው እየፈጸሙ ሳይሆን በቁርጥ ሃሳብ እና በፍፁም ልብ መመለስን ይጠይቃል።

በአንድ በኩል ውግዘቴን አሥነሳለሁ፣ ሥላጣነ ክህነቴን አስመልሳለሁ እየተባለ በሌላ በኩል በዚያው የለኝም ተወስዶብኛል በተባለው ክህነት መስቀል ይዞ እያሳለሙ፣ እየቀደሱ ፣ እያጠመቁ ለሦስት ዓመት ኖሮ አሁንም በዚያው ማዕርግ ነኝ የሚል መሪ አሁንም ተከታዮቹን እንደ ዋስትና እና እንደማስያዣ አድርጎ ለራስ ጥቅም መደራደሪያ ለማድረግ እንጂ የልብ መጸጸት እና መመለስ እንደሌለው ያሳያል።

ጥፋትን አምኖ እና ተጸጽቶ የመጣን ሁሉ ግን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷን መመሪያ በማድረግ መጸጸቱትና እና መመለሱን መዝና እንደሥርዓቱ ቀጥታ ወደ ቤቷ ትቀበለዋለች። ሆኖም ግን አሁንም በዚያው በቀደመው ኅሊና እና ማንነት ላይ ቆሞ ምሕረት እንዲሁ ይደረግልኝ ማለት ራስን ከማሞኘት ያለፈ  አይሆንም።ለዚህም በቂውን ጊዜ ወስዶ መመርመር ድርሻው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብቻ ነው።

ወደ እውነተኛው መንገድ መመለስን የመረጣችሁ ምእመናን ግን አሁንም በዚህ ውሳኔያችሁ ጸንታችሁ በአካባቢያችሁ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እንደማንኛውም ኦርቶዶክሳዎ ክርስቲያን አገልግሎት ማግኘት ባለመብት መሆናችሁን እንድትረዱት ጨምረን እናሳውቃችሁአለን።

nochange-page-001.jpg
nochange-page-002.jpg