የማቴዎስ ወንጌል

የማቴዎስ ወንጌል

የዚህ መልእክት ዋና አላማው በሃያ ስምንቱም ምዕራፎች ውስጥ ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በየትኛው ምዕራፎች ላይ እንደተጻፉ አንባቢ በቀላሉ እንዲረዳና ከብዙ ልምምድና ጥናት በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ትምህርቶች በውል ለማወቅ እንዲረዳ ነው። በዚህ ዓይነት መልኩ የመጽሐፍ ቅዱሱ አበይት ነጥቦች ለአንባብያን ቢዘጋጁም አንባብያን ግን ዘወትር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በመገናኘት ሙሉ ቃሉን ማንበብ ይጠበቅባቸዋል። ይኼኛው የትምህርት አሰጣጥና ማገናዘቢያ አዳዲስ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትንና ታዳጊ ወጣቶችን ለማስተማሪያ ታላቅ ጠቀሜታ አለው ብለን እናስባለን። ስለዚህም አንባብያን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ የተጻፉትን ዋና ዋና ነጥቦች በመመልከት በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትምህርቱ እንደተጻፈ ለመረዳት ዘወትር ለተወሰነ ሰዓት ማንበባችሁን አትዘንጉ።

PDF

Read More

ጸሎት ከመጽሐፍ ቅዱስ

ጸሎት ከመጽሐፍ ቅዱስ

1-  አባታችን ሆይ
2-  የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት - የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፩፤፵፯-፶፭
3-  የነቢዩ ዳንኤል ጸሎት - ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱፤ ፬-፲፱
4-  የነቢየ እግዚአብሔር የቅዱስ ዳዊት ጸሎት - መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፮ (፲፯)፤፩-፲፭
5-  ባዘነና ልመናውን በእግዚአብሔር ፊት ባፈሰሰ ጊዜ የችግረኛ ጸሎት - መዝሙር ፻፩(፻፪)
6-  የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር - ትንቢተ ዕንባቆም ፫፡፩-፲፮
7-  ጸሎተ ኤርምያስ - ሰቆቃወ ኤርምያስ ፭፡፩-፳፪
8-  የሕዝቅያስ ጸሎትና የጸሎቱ መልስ - ኢሳ. ፴፰፡፩-፳
9-  ጸሎተ ሐና - ፩ መጽ. ሳሙ. ፪፤፲
10- ጸሎተ ሙሴ - መዝ. ፺፡፩-፳-፲፯
11- የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎትና የእግዚአብሔር መልስ - ዘጸ. ፴፪፡፲፩-፲፮
12- ጸሎተ ነህምያ - ነህምያ ፩-፭-፲፩
13- የጠቢቡ ሰሎሞን ጸሎት - ፩ መጽ. ነገሥት ፰፡፳፪-፶፬
14- የነቢዩ ዮናስ ጸሎት - ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ ፪፤፫-፲

PDF

Read More

በምድረ ኢትዮጵያ የኖሩና ለኢትዮጵያ መጠሪያ የሆኑ ፤ የካም ልጆችና የልጅ ልጆች

በምድረ ኢትዮጵያ የኖሩና ለኢትዮጵያ መጠሪያ የሆኑ ፤ የካም ልጆችና የልጅ ልጆች

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3600 (ሦስት ሺህ ስድስት መቶ) ዓ.ዓ በየመን ይኖሩ ከነበሩ ከነገደ ሴም የተከፈሉ ራሳቸውን ነገደ ዮቅጣን በማለት በባብኤል መንደር (የመከራ በር) በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ ዮቅጣን አማርኛ መጠሪያቸው ሲሆን በግዕዝ ዮቃጤን በአውሮፓውያን የካታን ይባላሉ፡፡ ዮቅጣን አስራሶስት ልጆች የነበሩት ሲሆን መኖሪያቸው የነበረውም በእስያ ምድር ከሜሻ እስከ ፋርስ እስከ ምሥራቅ ተራራ ነበር (ዘፍ 10፡-በሙሉ) ከነዚህም ከአሥራ ሦስቱ ልጆች አምስቱ ሳባ፣ ይባል ፣አፈር ፣አሲማኤል፣ ኤውላጥ፣ ቦታ ስለጠበባቸው ከወንድሞቻቸው ተለይተው የእስያ ደቡብ ወደሚሆን ወደ የመን መጡ፡፡

የየመንም ብልሃትና ጥበብ ተምረው በመልካም ኑሮ ሲኖሩ የህንድ ነገሥታት ጦር እየሰደዱ የመንን እየወጉ ስላወካቸው ሶስቱ ሳባ ይባልና አፈር ሁለቱን ወንድሞቻቸው ጥለው የነገደ ካም ወገን ጰኦሪ 1ኛ በነገሠበት ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ገቡ፡፡ ከጥቂት ዘመናት በሁዋላ እነዚህ ሶስቱ ነገደ ዮቅጣን እርስ በእርሳቸው ካለመስማማታቸው የተነሣ ተለያይተው ለየብቻቸው ሀገር ያዙ የያዙዋቸው የሀገሪቱ ክፍሎችም ሳባ ትግሬን ይባል አዳልን ኦፈር ውጋዴንን ይዘው ቀርተዋል፡፡

Read More

አምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት (The Five Oriental Churches)

አምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት (The Five Oriental Churches)

አምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ ግብጽ፣ ሶሪያ፣ አርመንና ሕንድ ሲሆኑ መለያቸውም ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው በማለት ከመለካውያን የተለዩ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ነው፡፡ ይህም 325 .. በኒቅያ 381 .. በቁስጥንጥንያ 431 .. በኤፌሶን የተላለፈውን ውሳኔ በአንድ ድምፅ ያለመለያየት የተቀበሉ ሃገሮች ናቸው፡፡

ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ መስማማት ያቃታቸው ሮማውያን እና ግሪኮች አራት ጉባኤ አድርገዋል፡፡ ይህም ከፍተኛው ከሦስቱ ጉባኤያተ ጋር ሲደመር ሰባት ጉባኤ ይሆናል፡፡ እንግዲህ ካቶሊኮችና የምሥራቅ መለካውያን ለእነዚህ ለሰባቱ ጉባዔያት አንድ ናቸው፡፡ እኛ ግን የመጀመሪያዎቹን ሦስቱን በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያ እና በኤፌሶን የተደረጉትን ጉባኤያት ብቻ እንቀበላለን ከዚህ በኋላ ግን የሮማ ካቶሊክ ለብቻዋ ያደረገቻቸውን ጉባኤዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ መዝግባቸዋለች እነዚህ ጉባኤዎች አሥራ አምስት ናቸው፡፡ በኬልቂዶን ጉባኤ ከተወሰነው -ሕጋዊ ውሳኔ በኋላ የመላካውያንና የተዋሕዶዎች አቋም በዘመኑ ሁሉ በጠላትነትና በመነቃቀፍ ነበር፡፡

Read More

ስምንቱ ማርያሞች በመጽሐፍ ቅዱስ

ስምንቱ ማርያሞች በመጽሐፍ ቅዱስ

፩- ማርያም የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት፦
፪- መግደላዊት ማርያም፦
፫- ማርያም (የቢታንያዋ) የማርታና የአልዓዛር እኅት፦
፬- ማርያም የያዕቆብና የዬሳ እናት፦
፭- ማርያም የማርቆስ እናት፦
፮- ማርያም የቀልዬጳ ሚስት፦
፯- ማርያም የሙሴና የአሮን እኅት፦
፰- ማርያም ከካሌብ ጎሳ የነበረችው፦

PDF

Read More