ስምንቱ ማርያሞች በመጽሐፍ ቅዱስ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያም በመባል የሚታወቁ ስሞችና ጥቅሶቻቸው የሚገኙበት ቦታ፦

፩- ማርያም የጌታችን የአምላካችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት፦
-    ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ስለመገኘትዋ ለዬሴፍም የጌታ መልአክ በሕልም   እንደታየው፦ ማቴ. ፩፥ ፲፰-፳፭
-    መልአኩ ገብርኤል እንዳበሠራት ወደ ኤልሳቤጥም ዘንድ እንደሄደች ኤልሳቤጥም እንደ ተሳለመቻት፦ ሉቃ. ፩፥ ፳፮-፶፮
-    በቃና ዘገሊላ ስለነበረው ድንቅ ተዓምራት፦ ዮሐ. ፪፥፩-፲፪
-    እናትህና ወንድሞችህ በውጭ ቆመዋል ብለው የተናገሩትና የመለሰላቸው መልስ፦ ማር. ፫፥፴፩-፴፭
-    ከሕዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው እንዳለችው፦ ሉቃ. ፲፩፥፳፯-፳፰
-    በመስቀሉ አጠገብ ቆማ እንደነበር፦ ዮሐ. ፲፱፥ ፳፭-፳፯
-    ከሐዋርያት ጋር አብራ በጸሎት ትተጋ እንደነበር፦ ሐዋ. ፩፥ ፲፬

፪- መግደላዊት ማርያም፦
-    ከሌሎች ሴቶች ጋር ጌታን ታገለግል እንደነበር፦ ሉቃ. ፰፥፪
-    በስቅለቱ ጊዜ፦ ማር. ፲፭፥፵    ማቴ. ፳፯፥፶፮    ዮሐ. ፲፱፥፳፭
-    በቀብሩ ጊዜ፦ ማር. ፲፭፥፵፯    ማቴ. ፳፯፥፷፩
-    በባዶው መቃብር፦ ማር. ፲፮፥፩-፲፩    ማቴ. ፳፰፥፩-፲        ሉቃ. ፳፬፥፲
-    በትንሣኤው ጊዜ፦  ማር. ፲፮፥፱    ዮሐ. ፳፥፩-፲

፫- ማርያም (የቢታንያዋ) የማርታና የአልዓዛር እኅት፦
-    አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሣውና ማርታና ማርያም እንዳነጋገሩት፦     ዮሐ. ፲፩፥ ፩-፵፬
-    በከበረ የናርዶስ ችቱ የኢየሱስን እግር እንደቀባች፦     ዮሐ. ፲፪፥ ፩-፰

፬- ማርያም የያዕቆብና የዬሳ እናት፦
-    በገሊላ ሳለ ያገለግሉትና ይከተሉት ከነበሩት አንዷ፦ ማር. ፲፭፥፵-፵፩
-    በስቅለቱ በቀብሩና በባዶው መቃብር ጊዜ፦ ማር. ፲፭፥፵፯ ማር. ፲፮፥፩-፰  ማቴ. ፳፯፥፶፮ ማቴ. ፳፰፥፩-፰ ሉቃ. ፳፬፥፩-፲
፭- ማርያም የማርቆስ እናት፦
-    ጴጥሮስ በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን በወኅኒ ሳለ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ብዙዎች ጸሎት ያደርጉ እንደነበርና ጴጥሮስም በእግዚአብሔር መልዓክ አማካኝነት ከወኅኒ እንደወጣ የሚገልጽ፦ ሐዋ. ፲፪፥፩-፲፫      
ሐዋ. ፲፪፥፲፪ (የማርቆስ እናት ማርያም)

፮- ማርያም የቀልዬጳ ሚስት፦
-    በጌታ መስቀል ሥር እንደነበረች፦ ዮሐ. ፲፱፥ ፳፭
፯- ማርያም የሙሴና የአሮን እኅት፦
-    ሕፃን ሙሴን በባሕር ተጥሎ ሳለ ትከታተለችው እንደነበር፦ ዘጸ. ፪፥ ፬-፰
-    ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ ስለመዘመርዋ፦ ዘጸ. ፲፭፥ ፳-፳፩ ሚክ. ፮፥፬…በፊትህ ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር
-    ሙሴ ኢትዬጵያዊቷን ስላገባ እንዳጉረመረመችና በለምፅ እንደተመታች፦ ዘኁ. ፲፪፥ ፩-፲፭ ዘዳ. ፳፬፥ ፱ አምላክህ…በማርያም ላይ ያደረገውን አስብ
-    ማርያም በቃዴስ ምድረ በዳ እንደሞተች፦ ዘኁ. ፳፥ ፩
፰- ማርያም ከካሌብ ጎሳ የነበረችው፦
-    ዮቴር ማርያምን ስለ መውለዱ፦     መጽ. ዜና ቀዳማዊ. ፬፥፲፯