የማቴዎስ ወንጌል

የዚህ መልእክት ዋና አላማው በሃያ ስምንቱም ምዕራፎች ውስጥ ያሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በየትኛው ምዕራፎች ላይ እንደተጻፉ አንባቢ በቀላሉ እንዲረዳና ከብዙ ልምምድና ጥናት በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ትምህርቶች በውል ለማወቅ እንዲረዳ ነው። በዚህ ዓይነት መልኩ የመጽሐፍ ቅዱሱ አበይት ነጥቦች ለአንባብያን ቢዘጋጁም አንባብያን ግን ዘወትር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በመገናኘት ሙሉ ቃሉን ማንበብ ይጠበቅባቸዋል። ይኼኛው የትምህርት አሰጣጥና ማገናዘቢያ አዳዲስ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትንና ታዳጊ ወጣቶችን ለማስተማሪያ ታላቅ ጠቀሜታ አለው ብለን እናስባለን። ስለዚህም አንባብያን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ የተጻፉትን ዋና ዋና ነጥቦች በመመልከት በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ትምህርቱ እንደተጻፈ ለመረዳት ዘወትር ለተወሰነ ሰዓት ማንበባችሁን አትዘንጉ።

PDF