አምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት (The Five Oriental Churches)

አምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተብለው የሚጠሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ ግብጽ፣ ሶሪያ፣ አርመንና ሕንድ ሲሆኑ መለያቸውም ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው በማለት ከመለካውያን የተለዩ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ነው፡፡ ይህም 325 .. በኒቅያ 381 .. በቁስጥንጥንያ 431 .. በኤፌሶን የተላለፈውን ውሳኔ በአንድ ድምፅ ያለመለያየት የተቀበሉ ሃገሮች ናቸው፡፡

ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ መስማማት ያቃታቸው ሮማውያን እና ግሪኮች አራት ጉባኤ አድርገዋል፡፡ ይህም ከፍተኛው ከሦስቱ ጉባኤያተ ጋር ሲደመር ሰባት ጉባኤ ይሆናል፡፡ እንግዲህ ካቶሊኮችና የምሥራቅ መለካውያን ለእነዚህ ለሰባቱ ጉባዔያት አንድ ናቸው፡፡ እኛ ግን የመጀመሪያዎቹን ሦስቱን በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያ እና በኤፌሶን የተደረጉትን ጉባኤያት ብቻ እንቀበላለን ከዚህ በኋላ ግን የሮማ ካቶሊክ ለብቻዋ ያደረገቻቸውን ጉባኤዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ መዝግባቸዋለች እነዚህ ጉባኤዎች አሥራ አምስት ናቸው፡፡ በኬልቂዶን ጉባኤ ከተወሰነው -ሕጋዊ ውሳኔ በኋላ የመላካውያንና የተዋሕዶዎች አቋም በዘመኑ ሁሉ በጠላትነትና በመነቃቀፍ ነበር፡፡

ከኬልቄዶን ውሳኔ በኋላ እኛም እነሱን ንስጥሮሳውያን መለካውያን ሁለት ባሕርይ ባዮች እንላቸዋለን፡፡ እነሱም እኛን የአውጣኪ ደጋፊዎች አንድ ባሕርይ ባዮች (MONOPHYSITE) ይሉናል፡፡ አንድ ባሕርይ የሚሉንም ከሁለት መናፍቃን ጋር አጣምረው ነው፡፡

1. የእግዚአብሔር ቃል ሥጋን እንጂ ነፍስን አልተዋሃደም ከሞል ከአቡሊናርዮስ ጋር አዛምደው ነው፡፡ በእነሱ አባባል ክርስቶስን አንድ ባሕርይ የሚለው ትምህርት የአቡሊናርዮስ ነው ቄርሎስም አንድ ባሕርይ ማለቱ ሳይጠነቀቅ ቀርቶ ነው ይላሉ፡፡

2. ቃልና ሥጋ በተዋሃዱ ጊዜ ቃል ሥጋን መጦታል፣ ለውጦታል ከእሳት እንደገባ ቅቤ አቅልጦታል ከሚለው ከአውጣኪ ጋር አዛምደው ነው፡፡ ግሪኮች ዛሬም እኛን ባዩ ቁጥር አንድ ባሕርይ ባዮች ናችሁ ይሉናል፡፡ ሌሎች ግን አምስቱንም የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት በተንኮል ለመከፋፈልና ለመለያየት የእኛን ተማሪዎችና መነኮሳት ሲያገኙ ሌሎች ናቸው እንጂ እናንተ ምኖፊስት አይደላችሁም በማለት የአንዳንድ የዋሆችን ልቡና ከፋፍለውታል በተለይም እኛ ኢትዮጵያን ከራሳችን ሊቃውንት የተፃፉ መጽሓፍትን ሳንመለከት ወደ ውጭ ስለምንላክ እነርሱ የሚሉን እውነት የሚመስለን ብዙዎች ነን፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ የግብጽ፣ የሶሪያና የአርመን እና የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አብያተ ክርስቲያናት ክርስቶስን አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው በማለት ከኬልቄዶን ጉባኤ የተለዩ ናቸው፡፡ ክርስቶስን አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው የምንለው አንደ አቡሊናርዮስ ከፍለን ቀንሰን አይደለም፡፡ እንደ አትናቴዎስ፣ እንደ ቄርሎስ፣ እንደ ዲዮስቆሮስ፣ አንድ አካል፣ አንድ ባሕርይ ባዮች ስንባል አንቆጣም በዲዮስቆሮስ አባትነት በአንድ ባሕርይ እምነት አናፍርምና፡፡

እዚህ ላይ ሳንጠቅስ የማናልፈው እስራኤል ለምን ከእነዚህ ከአምስቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ጋር አብራ አልተጠቀሰችም የሚለውን ሲሆን ምላሹ በጉባኤ ኬልቄዶን በተነሳው በንስጥሮሳዊያን ጉባኤ (ይኸውም ይህ ጉባኤ በንስጥሮሳዊነት ሲያለሙት የሚኖሩ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነሱም -

/ 431 .. በኤፌሶን በንስጥሮሳዊነታቸው የተወገዙ ሰዎች ወደዚህ ጉባዔ እንዲመለሱ መደረጉ
/ የልዮን ጦማር /ደብዳቤ/ ያዘለው መልእክት ግልጥ ያለ ንስጥሮሳዊ ስለሆነ ነው፡፡

የምንፍቅና የጥርጥር የክህደት ትምህርት የተነሣ እነዚህ አምሥቱ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የተባሉ ሃገሮች በአንድ ድምፅ በመሆን ተቋውሟችውን ያሰሙ እና በሃይማኖትም በተጨማሪ ያላቸው ዶጎማና ቀኖና አንድ የሆኑ፣ ሰማንያ አንዱን መጽሐፍ ቅዱስ የተቀበሉ ከኤጲስ ቆጶስ እስከ ፓትሪያሪክ የሚመረጡ አባቶች በድንግልና፣ መንኩሰው በቁምስና ማዕረግ ያገለገሉ አባቶችን ለመሾም አንድ ለመሆናቸው አምሥቱ ምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት (The Five Oriental Churches) ተብለው በመጠራታቸው ነው፡፡

እስራኤል ግን ይህን ከማድረግ የተቆጠበች አንዲያውም ከተቃዋሚዎች (ከተጠራጣሪዎቹ) ጎን የቆሙም አልጠፉም በሃገሪቱም በውስጧ በተለያዩ እምነት ስር የነበረች የካቶሊክን፣ የመለካውያንን እምነት ተቀበለች፤ የሁሉም ሃይማኖት አራማጅ የነበረች ሃገር ናት፡፡ እንዲሁም በሥጋ ማርያም ተገልጦ የመጣውን ወልደ እግዚአብሔር አልቀበልም በማለት እስከ መስቀል ሞት ያደረሰች ሃገር በመሆኗ ነው፡፡ ‹‹የእርሱ ወደሆኑት መጣ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም›› ሲል ቅዱስ ዮሐንስ የተናገረውም ከዚህ መነሻነት ነው፡፡ (ዮሐ 111) ሌላው እስራኤል ከጉባኤያቱ ላይ ራሱን የቻለ መንበር ያልነበራት ሃገር ስትሆን በወኪል የምትመራ ሃገር በመሆኗ ከአምስቱ የምሥራቅ አብያተክስትናት ጋር በአንድ (አብራ) አልተጠቀሰችም፡፡